4 ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች ከተረጂነት ወደ ትርፍ አምራችነት ተሸጋግረዋል
++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ባለፉት ዓመታት በግብርናው መስክ በተከናወኑ ተግባራት ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ዜጎች ከተረጂነት ተላቀው ወደ ትርፍ አምራችነት መሸጋገራቸውን የግብርና ሚኒስትር አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አዘጋጅነት “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት” በሚል መሪ ሐሳብ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
የግብርና ሚኒስትር ዴአታ ፍቅር ረጋሳ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደተናገሩት፣ የኢትዮጵያ ግብርና በዝናብ ጥገኝነት ላይ የተመሠረተ ስለነበረ፤ የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ፈተና ሆኖ ቆይቷል።
የግብርናው ዘርፍ ከአምስቱ የኢኮኖሚ ማዕዘናት አንዱ በማድረግ ታሪክ ቀያሪ የሆኑ ኢኒሼቲቮች ተግባራዊ ተደርገዋል ያሉ ሲሆን፤ ኢኒሼቲቮቹ የምግብ እና ሥነ-ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፤ ከውጭ የሚገቡ የግብርና ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት፤ የወጪ ንግድ አቅም ማሳደግ እና የሥራ ዕድሎችን መፍጠር ዓላማ ያደረጉ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራት በእርሻ እና እንስሳት ዘርፍ የተገኘው ውጤት በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች በምግብ ራሳቸውን እንዲችሉ አድርጓል ያሉት ሚኒስትር ዴታው፤ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች በመሥራት የድርቅ ተጋላጭነትን የመቀነስ እና የመስኖ አውታሮችን በብዛት የመገንባት ስራ መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
እንደ ሚኒስትር ዴታው ማብራሪያ፤ “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት” በሚል በተከናወነው ሀገር አቀፍ ንቅናቄ 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች ከችግር መላቀቅ ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን የምግብ ዋስትና ጥረት በማገዝ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረጉ ይገኛሉ። እነዚህ ስራዎች በዓለም አቀፍ መድረኮች ለኢትዮጵያ እውቅና እያስገኙ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
በአብዱረዛቅ መሐመድ
Post #46443
2.6K



- 😁 3
- ❤ 1