ዜና: በ #ኢትዮጵያና በ #ኤርትራ መካከል ውጥረት በተባባሰበት በዚህ ሰአት፣ የ #ኤርትራ ሠራዊት ትግራይ ክልል #አዲግራት አካባቢ መስፈሩ ተዘገበ
የኤርትራ ሰራዊት አባላት በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በሚገኙ የተወሰኑ አካባቢዎች ገብተዋል ሲሉ የአካባቢው ባለስልጣናትና ነዋሪዎች ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) ተናገሩ። የኤርትራ ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱ ወታደሮች በአዲግራትና አካባቢዋ እንዲሁም ወደ ደቡብ አቅጣጫ ወደ #መቀሌ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው ተግልጿል።
በአዲግራት የሚገኙ አንድ የአካባቢው ባለስልጣን ለአኤፍፒ እንደገለጹት፣ የኤርትራ ወታደሮች በከተማዋ ውስጥ ለቀናት የቆዩ ሲሆን ይህም በነዋሪዎች ዘንድ ስጋት ፈጥሯል። አንድ የዓይን እማኝ የኤርትራ ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱ ወታደሮች በዋናው መንገድ ወደ ደቡብ ሲንቀሳቀሱ ማየታቸውን የተናገሩ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ በየኤርትራ ኃይሎች በከባድ መኪኖችና በፓትሮል ተሽከርካሪዎች ከአዲግራት በስተደቡብ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው ዕዳጋ ሐሙስ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=14633
Post #9232
4.14K
