TGViewer
Channel ✦ Verified Channel
Addis Standard Amharic

Addis Standard Amharic

@addisstandardamh

አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Subscribers
21.4K
Photos
6.4K
Videos
141
Links
5K
Recent Posts 20 shown
Post #9273 837
“ፍትሕና እኩልነት ለሰው ልጅ ያላቸው ዋጋ ከምግብ፣ ከመጠጥና ከልብስ ፍላጎት ያልተናነሰ ነው” - ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
Post #9271 1.37K
ዜና: በ #አማራ ክልል ግጭት በተባባሰበት ወቅት የቦረና ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ መገደላቸው ተገለፀ

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባባቢዎች በመንግሥት እና በታጣቂዎች መካከል ግጭት በተባባሰበት ወቅት በደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ የሆኑት ኢንስፔክተር ጋሻው ካስየ ከበደ መገደላቸውን ተገለፀ።

የቦረና ወረዳ ኮሙኒኬሽን ትላንት ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. ባወጣው የሀዘን መግለጫ ኢንስፔክተር ጋሻው መስከረም 30/2019 ዓ.ም. በህግ ማስከበር ዘመቻ እያሉ ህይወታቸው ማለፉን አስታውቋል።

መግለጫው የገዳዮች ማንነት እና ስለ ክስተቱ ዝርዝር መረጃ ባይሰጥም፤ “ኢንስፔክተር ጋሻው ካስየ ከበደ መስከረም 30/2019 ዓ.ም በህግ ማስከበር ዘመቻ እያሉ በጀግንነት ለሀገራችውና ለህዝባቸው ሲሉ በክብር ተሰውተዋል” ብሏል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=14805
Post #9270 1.8K
ዜና: “ፍትሕና እኩልነት ለሰው ልጅ ያላቸው ዋጋ ከምግብ፣ ከመጠጥና ከልብስ ፍላጎት ያልተናነሰ ነው” - ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

የ #ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም በተከፈተው ዓመታዊ የጠቅላላ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፣ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የሚታዩ የአስተዳደር፣ የፍትሕና የእኩልነት እጦት ችግሮችን በግልጽ በመኮነን ዘመናዊ አሰራር እንዲዘረጋ ጥሪ አቀረቡ።

ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ወቅት እንደገለጹት፣ በማኅበረሰብም ሆነ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ የፍትሕና የእኩልነት አስፈላጊነት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=14818
Post #9269 2.05K
ትንታኔ፡ የትምህርት ሥርዓትን ከአውሮፓውያን አስተሳሰብ ነፃ ማድረግ በ #ኢትዮጵያ - በገሃድ እየተቀየረ ያለው ምንድን ነው?

ለተማሪዎች የትምህርት ማሻሻያ በትምህርት ሚኒስቴር የፖሊሲ ሰነዶች ላይ ብቻ የሚገኝ ነገር አይደለም። ይልቁንም በሚማሩት ትምህርት፣ በሚማሩበት መንገድ፣ እንዲያውቁ በሚጠበቅባቸው መጠን፣ እንዲሁም ባህላቸውን እና ማህበረሰባቸውን በክፍል ውስጥ ማየት መቻላቸው ላይ የሚለማመዱት እውነታ ነው።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሦስተኛ ዓመት ተማሪ ለሆነ አንድ ወጣት፤ የኢትዮጵያ የአሁኑ የትምህርት ካሪኩለም የኢትዮጵያን ባህል እና እሴቶች በአግባቡ አያንጸባርቅም። ችግሩ በክፍል ውስጥ ከሚገለጠው ቋንቋ በላይ እውቀት እራሱ በሚተላለፍበት መንገድ ላይ እንደሆነ ተማሪው ይሞግታል።

አንዳንድ የማስተማር መንገዶች የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታዎች በበቂ ሁኔታ አያሳዩም፤ የሃይማኖት ትምህርትን ጨምሮ የቀደሙት የእውቀት ማስተላለፊያ ባህሎችን እውቀት ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፍባቸው እንደነበሩ ማሳያ አድርጎ የሚያቀርብ ሲሆን፤ ዓለም አቀፋዊነት (Globalization) እኚህን አሰራሮች እንዲዳከሙ አስተዋጽኦ ማድረጉን ይሞግታል።

የሁለተኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነ ሌላ ወጣት ደግሞ ጽንፍ ያልያዘ ምልከታ ያቀርባል። የኢትዮጵያ የታሪክ እና የእሴት ስብስብ በካሪኩለሙ ውስጥ መካተቱን እያመነ፤ የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት አወቃቀር ግን ምዕራባዊ እንደሆነ ይገልጻል።

ሙሉ ትንታኔውን ያንብቡ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=14802
Post #9268 2.28K
#ዕለታዊ_ዜና፡ #ቻይና ሳውዘርን ኤርላይንስ #ቻንግሻ በኩል #ጉዋንግዡን ከ #አዲስ_አበባ የሚያገናኝ አዲስ የበረራ አገልግሎት ጀመረ

ቻይና ሳውዘርን ኤርላይንስ በቻንግሻ በኩል የቻይናዋን ጉዋንግዥው ከተማ ከኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ጋር የሚያገናኝ አዲስ የጉዞ መስመር በመክፈት በቻይና እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የበረራ አገልግሎት ትስስር እንዲጨምር ማድረጉ ተዘገበ።

የቻይና መንግሥታዊ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት የመጀመሪያው በረራ ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. ተካሂዷል።

https://addisstandard.com/Amharic/?page_id=14361
Post #9267 2.4K
#ዕለታዊ_ዜና: የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ባጋጠመው የገንዘብ እጥረት በ #ኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ምዝገባን አቋረጠ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ያጋጠመውን ዓለም አቀፍ የገንዘብ እጥረት ተከትሎ፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ ከሱዳን እና ኤርትራ የመጡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ምዝገባን መቋረጡን የድርጅቱ ዋና ኃላፊ ባርሃም ሳሊህ ሰኞ ዕለት ማስታወቃቸውን ሮይተርስ ዘገበ።

በጄኔቫ በተካሄደው የድርጅቱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ሳሊህ፣ የሰደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ለ2026 (እ.ኤ.አ) የሥራ ማስኬጃ ከሚያስፈልገው 8.5 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ማግኘት የተቻለው 3 ቢሊዮን ዶላር ወይም 35 በመቶውን ብቻ መሆኑን ገልጸዋል። 

https://addisstandard.com/Amharic/?page_id=14361
Post #9266 2.32K
#ዕለታዊ_ዜና፡ #እስራኤል #የኢንዶኔዥያ ፓይለት አለበት የተባለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን ከበረራው እንዲመለስ አደረገች

እሑድ መስከረም 30  ለሰኞ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ምሽት ወደ እስራኤል ቤን ጉሪዮን አየር ማረፊያ ይጓዝ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን፣ የእስራኤል ባለሥልጣናት ከአውሮፕላኑ የበረራ አባላት መካከል የኢንዶኔዥያ ዜጋ መኖሩን ካወቁ በኋላ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ መደረጉን «ቻናል 13» እና ሌሎች በርካታ የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።

አውሮፕላኑ የአየር ላይ በረራ በጀመረ በአንድ ሰዓት ገደማ ጊዜ ውስጥ የእስራኤል የደኅንነት ባለሥልጣናት የበረራ አባላቱን ዝርዝር ከደረሳቸው በኋላ፣ ከፓይለቶቹ አንዱ የኢንዶኔዥያ ዜጋ መሆኑን በማወቃቸው የወሰዱት እርምጃ መሆኑም ተጠቅሷል።

https://addisstandard.com/Amharic/?page_id=14361
Post #9265 2.6K
#ዕለታዊ_ዜና: በ #ደቡብ_ሱዳን ሌክስ ግዛት በተቀሰቀሰ ግጭት 70 ገደማ ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ

በደቡብ ሱዳን ሌክስ ግዛት ውስጥ በሚገኙ የተቀናቃኝ ማህበረሰቦች ታጣቂ ወጣቶች መካከል በተከሰተ ግጭት አራት ወታደሮችን ጨምሮ 70 ሰዎች መሞታቸውን እና ከአስር በላይ መቁሰላቸውን የከተማው ባለሥልጣናት ለአሶሼትድ ፕሬስ (AP) ገለጹ።

ግጭቱ የተከሰተው ዓርብ ዕለት በሮምቤክ አካባቢ ሲሆን፣ የመንግሥት ኃይሎች እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም አስከባሪዎች ፀጥታ ለማስከበር ጥረት አድርገዋል።

https://addisstandard.com/Amharic/?page_id=14361
Post #9264 3.31K
#ትኩስ_ዜና፡ በ #ኢትዮጵያና #ኤርትራ መካከል ውጥረት እየጨመረ ባለበት በዚህ ሰአት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከ #እስራሉ ኔታንያሁ ጋር በስልክ ተወያዩ

በኢትዮጵያ እና በጎረቤት ኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት እየጨመረ በሄደበት ወቅት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በስልክ መወያየታቸውን ገለጹ።

ይህ የስልክ ውይይት የተካሄደው፣ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ እና በእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዴኦን ሳር መካከል ከተደረገው ተመሳሳይ የስልክ ውይይት ከአንድ ሳምንት ከሳምንት በኋላ ነው።
https://addisstandard.com/Amharic/?page_id=14361
Post #9263 3.23K
#ዕለታዊ_ዜና: በ #ኢትዮጵያ እና #ኤርትራ መካከል ውጥረት በተባባሰበት ወቅት #ሶማሊያ ገለልተኛ መሆኗን ገለጸች
Post #9262 3.15K
ዜና: የ #ቀይ_ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በ #ኢትዮጵያ #አፋር ክልል ባካሄደው ጉባኤ #ፕሬዝዳንት_ኢሳይያስ እና መንግሥታቸው “ለፍትሕ” እንዲቀርቡ ጠየቀ

የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ቀባአዴድር / RSADO) በአፋር ክልል ሎጊያ ከተማ ዛሬ ያካሄደውን ሕዝባዊ ጉባኤ ሲያጠናቅቅ፣ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ እና ገዢው የሕዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲና ፍትሕ (ህግደፍ) መንግሥት በቀይ ባሕር አፋር ሕዝብ ላይ ፈጽመውታል ላለው ሰብአዊ ጥሰትና ውድመት ተጠያቂ እንዲሆኑና ለፍትሕ እንዲቀርቡ ጥሪ አቀረበ።

ይህ ጉባኤ ድርጅቱ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ሲያካሂዳቸው የቆያቸው የፖለቲካና የወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ሲሆን፤ የተካሄደውም የተካሄደውም በኢትዮጵያና በ #ኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በጨመረበት ወቅት ነው።

ድርጅቱ ዓለም አቀፍ ትኩረት ለማግኘትም ጥረት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፣ በቅርቡም #የእስራኤልን እገዛ ለማግኘት መሪዎቹ ያከናወኗቸው እንቅስቃሴዎች በእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ጭምር ሽፋን አግኝተዋል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=14789
Post #9261 3.09K
#ዕለታዊ_ዜና: በ #ጅቡቲ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ በርካታ #ኢትዮጵያውያን የጫነ ጀልባ በመስጠሙ ቢያንስ 139 ስደተኞች ሕይወት ማለፉ እና 84 ሰዎች መጥፋታቸው ተገለጸ

ወደ የመን ለመጓዝ 305 ሰዎችን የጫነች ጀልባ በጂቡቲ የባሕር ዳርቻ በመስጧ አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ዜጎች የሆኑ ቢያንስ የ139 ስደተኞች ሕይወት ማለፉን እና ሌሎች 84 ሰዎች መጥፋታቸውን የዓለም የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) እሑድ ዕለት አስታወቀ።

የድርጅቱ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ጀልባዋ የሰመጠችው መስከረም 28 እና 29 ሌሊት በኦቦክ የባሕር ዳርቻ ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ ሲሆን፣ ይህ አደጋም በባብ አል-መንደብ ሰርጥ ላይ ከተመዘገቡት እጅግ አሰቃቂ የባሕር አደጋዎች አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

ዓለም የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) እንደገለጸው፣ 82 ሰዎች ከአደጋው በሕወት የተረፉ ሲሆን ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች ናቸው።

https://addisstandard.com/Amharic/?page_id=14361
Post #9260 3.14K
ዜና ትንታኔ፡ በ #ደቡብ_ትግራይ ራያ አለማጣ ውጥረት ተባባሰ፤ #አብን የትግራይ ሰላም ኃይልን ሰብዓዊ ጥሰቶች በመፈፀም ከሰሰ

የ #አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከጸጥታና ከአስተዳደር ቁጥጥር ጋር ተያይዞ የታጠቁ ኃይሎችን እና የፌዴራል ኃይሎችን ያካተተ ግጭት መከሰቱን ተከትሎ፣ የትግራይ ሰላም ኃይል (ቲፒኤፍ) በራያ አለማጣና አካባቢው ግድያዎችን መፈጸሙን፣ ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ያሉ ተፈናቃዮች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን እና የፖለቲካዊና አስተዳደራዊ የበላይነት ለመጫን መሞከሩን ገለፀ።

አብን ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ኃይሎች ከወጡ በኋላ የትግራይ ሰላም ኃይል ወደ ራያ አለማጣ መግባቱ ለዓመታት መፈናቀልና ግጭት ለተጋፈጡ ነዋሪዎች “አዲስ የጸጥታ ችግር ምዕራፍ” ከፍቷል ብሏል።

ፓርቲው የፌዴራል መንግሥት የትግራይ ሰላም ኃይልን ከአካባቢው “እንዲያስወጣ” እና አካባቢያዊ ጊዜያዊ አስተዳደር እስኪቋቋም ድረስ የጸጥታ ማስከበር ኃላፊነቱ የፌዴራል ኃይሎች ብቻ እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=14782
Post #9259 3.31K
#ዕለታዊ_ዜና: በ #ኢትዮጵያ እና #ኤርትራ መካከል ውጥረት በተባባሰበት ወቅት #ሶማሊያ ገለልተኛ መሆኗን ገለጸች

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ውጥረት እያባባሰ ባለበት ወቅት ሶማሊያ ገለልተኛ ሆና እንደምትቀጥል በመግለፅ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ያገረሸው ግጭት በመላው የአፍሪካ ቀንድ ሰፊ የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ቀውሶችን ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቃለች።

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ለቢቢሲ ሶማሊ በሰጡት ቃለ ምልልስ መቃዲሾ ከሁለቱም ሀገራት ጋር መልካም ግንኙነት እንዳላት እና በአለመግባባታቸው ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌላት ገልጸዋል።

https://addisstandard.com/Amharic/?short_news=n-14778
Post #9258 3.24K
#አዲስ_አበባ ራሷን እንደምትከላከል መግለጿን ተከትሎ #ኤርትራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀች
Post #9257 3.42K
#ዕለታዊ_ዜና: በ #ግብፅ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ የ #ሱዳን ወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት ቢያንስ 200 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በግብፅ ድንበር አቅራቢያ በስተሰሜን ምስራቅ ሱዳን በሚገኙ አነስተኛ የባህላዊ ወርቅ ማዕድን ማውጫ አካባቢዎች ላይ ቅዳሜ ዕለት በተፈጸመ የአየር ጥቃት ቢያንስ 200 ሰዎች መገደላቸውን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን «ሱዳን ትሪቢዩን» የተረፉ ሰዎችን ዋቢ በማድረግ ዘገበ። የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት መኖሩም ተነግሯል።

ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች ለዜና ወኪሉ እንደገለፁት፣ ጥቃቱ በዕለቱ ንጋት 11 ሰዓት አካባቢ በቀይ ባህር ግዛት ውስጥ በሚገኘው ሻማል አል-ዋዲ የማዕድን ማውጫ ላይ ተፈፅሟል። በወቅቱ ማዕድን አውጪዎች የጠዋት ስራቸውን ለመጀመር እየተዘጋጁ እና ሌሎችም ከምድር በታች እንደነበሩ ገልፀዋል።

https://addisstandard.com/Amharic/?page_id=14361
Post #9256 3.38K
ዜና: #አዲስ_አበባ ራሷን እንደምትከላከል መግለጿን ተከትሎ #ኤርትራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀች

የኤርትራ መንግስት አዲስ አበባ የኤርትራ ኃይሎች ትግራይን ወረዋል ስትል ያቀረበችውን ውንጀላ «የጦርነት አዋጅ» ሲል ሲሆን በመግለፅ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጥሪ አቀረበ። ይህ ጥሪ የቀረበው ኢትዮጵያ አሥመራ "ወረራ ፈጽመብኛለች" በማለት መክሰሷን እና ራሷን እንደምትከላከል ማስጠንቀቋን ተከትሎ ነው።

የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳለህ ቅዳሜ ዕለት ለፀጥታው ምክር ቤት በጻፉት ደብዳቤ፣ የኤርትራ ኃይሎች በሰሜን ትግራይ እስከ 60 ኪሎ ሜትር ዘልቀው ገብተዋል የሚለው የኢትዮጵያ ክስ የጦርነት እወጃ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ምክር ቤቱ ኢትዮጵያን እንዲያወግዝ እና ከተቃውሞ እስከ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ሊደርሱ የሚችሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስችለውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ምዕራፍ 7 ስር ያለውን ሥልጣን እንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=14761
Post #9255 3.64K
#ዕለታዊ_ዜና፦ በ #ሪያድ ንጉሥ ካሊድ አየር ማረፊያ ላይ በ #ሁቲዎች በተፈጸመ ጥቃት አንድ ሰው ሲሞት 11 ሰዎች ቆሰሉ

ትላንት እሁድ በሪያድ በሚገኘው የንጉሥ ካሊድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በሁቲ ታጣቂዎች በተፈጸመ አዲስ ጥቃት አንድ ሰው ሕይወቱ ሲያልፍ 11 ሰዎች መቁሰላቸውን ኤኤፍፒ (AFP) ዘገበ። ጥቃቱን ተከትሎ የሳዑዲ ባለሥልጣናት የአውሮፕላን ማረፊያውን ለተጨማሪ 24 ሰዓታት ዝግ አድረገዋል።

በ #ኢራን የሚደግፈው የ #የመኑ ሁቲ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ አውሮፕላን ማረፊያውን ጨምሮ ሳዑዲ አረቢያ ላይ ያነጣጠሩ በርካታ ጥቃቶችን መፈጸሙን አምኖ፣ በሀገሪቱ የመጓጓዣ ማዕከላት ላይ ተጨማሪ ጥቃቶችን እንደሚፈጽም ዝቷል።

https://addisstandard.com/Amharic/?page_id=14361
Post #9254 4.31K
#ዕለታዊ_ዜና፦ በ #ሱዳን #ብሉ_ናይል ክልል በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ አቅራቢያ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ ቢያንስ 30 ሰዎች ተገደሉ

በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት ውስጥ ከሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ አቅራቢያ በትናትናው እለት በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ ቢያንስ 30 ሰዎች መገደላቸውን የክፍለ ሀገሩ ባለሥልጣናት እና የዓይን እማኞች ገለጹ።

ጥቃቱ የተፈጸመው ከዳማዚን በስተምሥራቅ 50 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በምትገኘው በወድ አል-ማሂ አካባቢ በሚገኘው አቡ ሻንዲ አካባቢ (መዲና 6) ላይ ነው።

https://addisstandard.com/Amharic/?page_id=14361
Post #9253 4.23K
ዜና: #ኢትዮጵያ #ኤርትራ «ወረራ ፈጽማብኛለች» ስትል በከሰሰችበት እና ራሷን እንደምትከላከል ባሳታወቀችበት ወቅት የተባበሩት መንግሥታት እና #አሜሪካ ውጥረቱ እንዲረግብ ጥሪ አቀረቡ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና ከፍተኛ የአሜሪካ ሕግ አዉጪ ምክር ቤት አባላት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል እየተካረረ የመጣው ውጥረት በአስቸኳይ እንዲረግብ ጥሪ አቀረቡ። ጥሪው የቀረበው አዲስ አበባ አስመራ በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ክፍል «ሙሉ በሙሉ ወረራ» ፈጽማብኛለች ስትል ከከሰሰች እና ራሷን እንደምትከላከል ካስጠነቀቀች በኋላ ነው።

አንቶኒዮ በኢትዮጵያ ትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች እንደገና ያገረሸውን ግጭት አስመልክቶ ከፍተኛ ስጋታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ሁሉም ወገኖች «ወዲያውኑ ተኩስ እንዲያቆሙ» እና ፈራሚዎች በፌዴራል መንግሥት እና በትግራይ ሕዝብ ነጻነት ግንባር (ሕወሓት) መካከል ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን ጦርነት ባስቆመው የጥቅምት 2015 ዓ.ም የፕሪቶሪያ ስምምነት ማዕቀፍ ስር ወደ ውይይት እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=14753
Older posts →

About this channel

How can I read @addisstandardamh without a Telegram account?
TGViewer shows the public web preview Telegram publishes for Addis Standard Amharic: recent posts, photos, videos and the subscriber count, with no app, login or account.
How many subscribers does Addis Standard Amharic have?
Addis Standard Amharic (@addisstandardamh) has 21.4K subscribers on Telegram, refreshed roughly every 30 minutes.
Does Addis Standard Amharic know I viewed it here?
No. Public channel previews carry no viewer identity, and TGViewer has no accounts or tracking of what you look up.
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →