TGViewer
Channel Public Channel
Phenomenal pictures & graphic design

Phenomenal pictures & graphic design

@abpgd

FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Subscribers
1.08K
Photos
1.8K
Videos
8
Links
16

Showing posts older than #1862 · Back to latest

Older Posts 16 shown
Post #1848 536
እኔ የጥበብ ሰጪው #የመልዐኩ_የቅዱስ_ዑራኤል ልጅ ነኘ፡፡

የድሃ አደጉን ልን ስለተቀበለኘ
በአውደምረቱ በፍቅር አሳደገኘ
ከመቅደስህ ተክለህ መገብከኘ ህይወትን
አዘጋጅተኸኛል ለሰማይ መንግስት፡፡

ከአመታዊው ክብረ በዓል ላይ ያነሳኀቸውን ፎተቶዎች ጀባ ልበላችሁ ትወዷቸዋላችሁ😍፡፡

ሁሌም ከፍ ከፍ ከፍ በልልን የኛ አባት
እንወድሃለን ለዕዝራሱቱኤል የዕውቀትን ፅዋ እንዳጠጣኸው ለኛም ለልጆችህ ሁሉን የአለም ፈተናን የምናልፍበትን ጥበብን አድለን

መዳንን እንድወርስ ሞትን እንዳላይ
ትረዳኘ ነበረ ከኔ ሳትለይ
በመንገዴ ሁሉ ከፊቴ ቀደምክ
አማኑኤል ብዬ ጌታን እንዳመልክ

@jahABP ነኘ😍😍🙏🙏
Post #1846 25.1K
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

" #የተበላሸ_ማሞቂያ

ጨርሰው የማይሰሩ አሳሳቢ አይደሉም አይሰሩምና ብልሽት ያለባቸው ማሞቂያዎች ግን ሰውየው ሲሞክራቸው ይሰራሉ ልብሱን አውልቆ ሲገባ ያረጥባሉ፡፡ ዓይኑን መግለጥ ከመታጠቢያው መውጣት በማይችልበት ሰዓት ሙቀታቸቅን መስጠት ያቆማሉ፡፡

ሰውየው በአይኑ ሳሙና ገብቷልና ልብሱን ለመልበስ እንኳን ከውሃ ያለፈ ገላውም ሳሙና ብቻ ነውና ማሞቂያው ስለተበላሸ የፈራውን ቅዝቃዜ የፈራውን እንቅጥቅጥ በግድ ይጋፈጣል፡፡ በሙቀት ጀምሮ በቅዝቃዜ በመጨረሱ ይንቀጠቀጣል፡፡

የተበላሸ ማሞቂያ ሲገጥመን ሁል ጊዜ የወረት ያስታውሰናል በሙቀት ጀምሮ በቅዝቃዜ መጨረስ የዚህ ዓለም መገለጫ ሆኗል፡፡ በኡኡታ ሠርግ በግልግል ማሬ የሚለው ቃል እሬቴ በሚል....ይለወጣል፡፡

ጨርሰው ጨካኘ ፈጽመው ክፉ የሆኑትነ አንሞክራቸውም አንቀርባቸውም ብንቀርባቸውም ተጠንቅቀን ነውና አይጎዱንም፡፡

እነደተበላሸው ማሞቂያ በሙቀት ጀምረው በቅዝቃዜ የሚጨርሱ አረጋግተው ቀጥል የሚያንቀጠቅጡን ስሜት አልባ አድርገው ቀጥለው የሚያሳምሙ አስደስተው ቀጥሎ እትትትትት.....የሚያሰኙ ብዙዎች ናቸው፡፡


ፍፁም እስክንራቆት ያባበሉን ሌላ ማየት እስከማንችል ያወሩን በማይዘልቀው ሙቀታቸው ያታለሉን የትም መሄድ እንደማንችል ሲረዱ ይለዋወጣሉ፡፡ በረዶአቸውን ማዝነብ ይጀምራሉ፡፡

ስለተለወጡብን ሰዎች ከማሰብ ስለተለወጥንባቸው ማሰብ የተሻለ ነው፡፡ በሞቀው ሰላምታ ጀምረን ያኮረፍናቸው ፍፁም ሚስጥራቸውን ከሰማን በኀላ ገሸሽ ያልናቸው ሌላ ማየት ሲያቅታቸው አውረን የተለየናቸው አውላላ ሜዳ ላይ መሪ ፈልገው ሲንከራተቱ የሳቅንባቸው ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

ምናልባት ዛሬ ሰው የማይወጣልን ሰው ገፍተን ሊሆን ይችላል፡፡ የዛሬውን የሚመጥነን ቅጣት ነውና በሚደርስብን ልንደሰት ይገባል፡፡

ትላንትን መልሰን መኖር ቢያቅተን በንሰሐ ማደስ እንችላለን፡፡ እነዚያንም ሰዎች መካስ እንችላለን፡፡
የንሰሐ የይቅርታ ዘመን ዕድል ነውና ሊያልፈን አይገባም፡፡

#ዛሬም_ከተለዋዋጭ_ማንነት_እንጠበቅ፡፡

#ሰው_እንጂ_አካባቢውን_የምንመስል_እስስት_አይደለንም፡፡

ጌታ ሆይ እውነተኛ ፍቅርን እንዳንገፋ እባክህን እርዳን፡፡ "

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ
መልካም ምሽት

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #1845 635
"የተበላሸ ማሞቂያ"🤔🤔

👣👣👣👣ጠብቁኘማ
Post #1843 1.08K
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ሰውን_ሰው_ያደረገው

☞ሰውን ሰው ያደረገው ስራ አይደለም አህያም ይሰራል::


☞ሰውን ሰው ያደረገው ንግግር አይደለም በቀቀንም ይናገራል::


☞ሰውን ሰው ያደረገው እብደት አይደለም ውሻም ያብዳል::


☞ሰውን ሰው ያደረገው ብልሐትአይደለም ዶልፊንም ብልሕ ነው::


☞ሰውን ሰው ያደረገው እንባ አይደለም አዞም ያነባል::


☞ሰውን ሰው ያደረገው ጭንቀት አይደለም ፍየልም ይጨነቃል።


☞ሰውን ሰው ያደረገው ስለነገ ማሰቡ አይደለም ጉንዳኖችም ስለመጪው
ክረምት አስበው በበጋ በቂ ምግብ ያዘጋጃሉ።


☞ሰውን ሰው ያደረገው....አስተሳሰቡ እና አመለካከቱ መልካምነቱ ነው።
ሰውን ሰው ያደርገው እግዚአብሔር ብቻ ነው ምክንያቱም
መልካም ጥበብ እና ማስተዋል ከእግዚአብሔር ዘንድ ነውና።

ሁሌም መካሪ ከተገኘ ህይወት ቀላል ነው፡፡

@jahABP ነኘ መልካም ጊዜ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #1842 729
ሰውን ሰው ያደረገው...........🤔🤔🤔

ጠብቁኘማ👣👣👣👣👣
Post #1841 858
MedhaniteEphrem Tamiru
ለስለስስስስስ ባለ ሙዚቃ
ወደ ሞቅታ

ይህን ዘፈን የምትጋበዙ ሰዎች አክብሮቴ ላቅ ያለ ነው ፡፡ 🙏🙏😍😍😍
Post #1840 807
በዚህ ብርድ ለስለስ ያለ ሙዚቃ መስማት ሞቅ ያደርጋል ብዬ አስባለሁ፡፡

ይህን ሙዚቃ እያጣጣምኩት ነው

ይህን ሙዚቃ ለምትወዱት ሰው ብትጋብዙት በልባችሁ ትልቅ ቦታ እንዳለው ይረዳል ብዬ አስባለሁ ❤️😍🥰😘👨‍❤️‍👨👩‍❤️‍👨

ብርዱን ገለል በል እንበለው ለስለስስስስ

ጠብቁኘማ👣👣👣👣😊😍👍
Post #1839 786
አቦ መልካም በዓል መልካም በዓል ይሁንላችሁ የተቸገሩትን የምንረዳበት የምንተሳሰብበት በዓል ይሁንልን፡፡
Post #1838 24.4K
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

" #አትድገሙ

ክፉ ነገር በማሰብ ይጀምራል፡፡ በማድረግ ይደመደማል፡፡ ማሰብ ለክፋት ፅንሰቱ ማድረግ ልደቱ ነው፡፡ ክፉ ነገር በማድረግ እየተገለጠ ይመጣል፡፡ ክፉ ነገርን የጦር ኀይል የፍርድ ጽናት የቅጣት ብዛት አያስቆመውም፡፡ክፉ ማሰብ ባለቤቱን ይበክላል ክፉ መናገር የጎረቤትን ሰላም ያናጋል አዕምሮን ያቆሽሻል ክፉ ማድረግ ማድረግ ማህበረሰብን ይጎዳል ያፈናቅላል፡፡ ክፉን መድገም ያደነድናል፡፡

#ያለመውደቅን_ያህል_ወድቆ_መነሳት_ክብር_ነው፡፡

የማይወድቅ የለም መልዐክ ካልሆነ የማፀፀት የለም ሰይጣን ካልሆነ፡፡

መድገም ማስተጋባት ነው፡፡ የሌሎችን ክፋት ማወደስ ለክፋት በነፃ ማስታወቂያ መስራት ነው፡፡ ሳይከፍሉን በቅዱስ አደባባይ ርኩስ ማስታወቂያ መስራት ነው፡፡ አንድ ጊዜ ክፉ ነገርን ከሚፈፅሙለት ይልቅ ደግመው በሚያወሩለት ሰይጣን ይደሰታል፡፡ ኃጢያት በተግባር ከሚፈፅሙ በምኞትና በትዝታ የሚጨልጡ ይበዙለታል፡፡

ሰው ነንና ክፉ ነገር እናስብ ይሆናል አለመናገር መልካም ነው፡፡ ሰው ነንና ተናግረን ይሆናል አለማድረግ ግን የተሻለ ነው ሰው ነንና አድርገን ይሆናል አለመድገም ግን መልካም ነው፡፡ መድገም መስራት ብቻ ሳይሆን ማስተዋወቅም ነው፡፡ ነገሩን ደግሞ ማውራት አይገባም፡፡

አዝረከርካለው ያልነውን ጉዳይ አንሰራፍተነው ሊሆን ይችላል፡፡ መድገም ብዙ ደቀመዝሙርትን ያፈራል፡፡ "ክፉ ነገርን አትናገሩ ደግማችሁም አታውሩ" ለምን ስንል፡- ያደረገ ካለ ይደፍራል ያሰበ ካለይፈፅማል የጀመረ ካለ ብቻዬን አይደለሁም ይላል የፈራ ካለ ልብ ያገኛል አደራረጉ የጠፋው ካለ ስልቱን ያገኛል፡፡

ክፋ ነገርን እግዚአብሔር ይገስፅህ በማለት መቅበር ያስፈልጋል፡፡
ዝርዝር ማውራት ለሴጣን ስፖንሰር መሆን ነው፡፡ ይህን ለመገንዘብ መንፈሳዊ ሰው ብቻ ሳይሆን ጨዋ አስተዳደግም በቂ ነው፡፡

#እጅግ_ግልፅነት_እብደት_ነው፡፡

ሰይጣን ዋንኛ ስራ ጆሮን ማስለመድ ነው፡፡ ጆሮን ማስለመድ የፖለቲካ ትልቅ ስልት ነው፡፡ የክፉዎች ትልቅ መንገድ ነው፡፡ ጆሮ ከለመደው አፈፃፀሙ ቀላል ነው፡፡ የምንናገረውን ሰዎች ይለማመዱታል ማስደንበርን ነው የምንፈራው ከዛም የተለየ ነገር አለ፡፡

ብዙ ክፉ ድርጊቶች ሲወሩ ይብሳሉ፡፡
ዝርዝር የሚወራው የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ ዛሬ ግን አጋንትን እያስለፈለፉ ትምህርት እንሰጣለን እየተባለ ነው፡፡ የሐሰት አባት ከተባለው የእውነት መረጃ እየተፈለገ ነው፡፡ ስብከት ሲያልቅብን ወደዚህ መግባታችን ያሳዝናል፡፡"

"መጥፎን ነገር እንደምንጠላ የሚያረጋግጥልን ስራችን ብቻ ነው" እና ከክፉ እንራቅ መልካምነትን እንዝራ እላለሁ

@jahABP ነኘ አሰተያየታችሁን አድርሱኘ መልካም ጊዜ ተመኘሁ፡፡
😍😁👍🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Older posts →
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →