TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #1846 25.1K
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

" #የተበላሸ_ማሞቂያ

ጨርሰው የማይሰሩ አሳሳቢ አይደሉም አይሰሩምና ብልሽት ያለባቸው ማሞቂያዎች ግን ሰውየው ሲሞክራቸው ይሰራሉ ልብሱን አውልቆ ሲገባ ያረጥባሉ፡፡ ዓይኑን መግለጥ ከመታጠቢያው መውጣት በማይችልበት ሰዓት ሙቀታቸቅን መስጠት ያቆማሉ፡፡

ሰውየው በአይኑ ሳሙና ገብቷልና ልብሱን ለመልበስ እንኳን ከውሃ ያለፈ ገላውም ሳሙና ብቻ ነውና ማሞቂያው ስለተበላሸ የፈራውን ቅዝቃዜ የፈራውን እንቅጥቅጥ በግድ ይጋፈጣል፡፡ በሙቀት ጀምሮ በቅዝቃዜ በመጨረሱ ይንቀጠቀጣል፡፡

የተበላሸ ማሞቂያ ሲገጥመን ሁል ጊዜ የወረት ያስታውሰናል በሙቀት ጀምሮ በቅዝቃዜ መጨረስ የዚህ ዓለም መገለጫ ሆኗል፡፡ በኡኡታ ሠርግ በግልግል ማሬ የሚለው ቃል እሬቴ በሚል....ይለወጣል፡፡

ጨርሰው ጨካኘ ፈጽመው ክፉ የሆኑትነ አንሞክራቸውም አንቀርባቸውም ብንቀርባቸውም ተጠንቅቀን ነውና አይጎዱንም፡፡

እነደተበላሸው ማሞቂያ በሙቀት ጀምረው በቅዝቃዜ የሚጨርሱ አረጋግተው ቀጥል የሚያንቀጠቅጡን ስሜት አልባ አድርገው ቀጥለው የሚያሳምሙ አስደስተው ቀጥሎ እትትትትት.....የሚያሰኙ ብዙዎች ናቸው፡፡


ፍፁም እስክንራቆት ያባበሉን ሌላ ማየት እስከማንችል ያወሩን በማይዘልቀው ሙቀታቸው ያታለሉን የትም መሄድ እንደማንችል ሲረዱ ይለዋወጣሉ፡፡ በረዶአቸውን ማዝነብ ይጀምራሉ፡፡

ስለተለወጡብን ሰዎች ከማሰብ ስለተለወጥንባቸው ማሰብ የተሻለ ነው፡፡ በሞቀው ሰላምታ ጀምረን ያኮረፍናቸው ፍፁም ሚስጥራቸውን ከሰማን በኀላ ገሸሽ ያልናቸው ሌላ ማየት ሲያቅታቸው አውረን የተለየናቸው አውላላ ሜዳ ላይ መሪ ፈልገው ሲንከራተቱ የሳቅንባቸው ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

ምናልባት ዛሬ ሰው የማይወጣልን ሰው ገፍተን ሊሆን ይችላል፡፡ የዛሬውን የሚመጥነን ቅጣት ነውና በሚደርስብን ልንደሰት ይገባል፡፡

ትላንትን መልሰን መኖር ቢያቅተን በንሰሐ ማደስ እንችላለን፡፡ እነዚያንም ሰዎች መካስ እንችላለን፡፡
የንሰሐ የይቅርታ ዘመን ዕድል ነውና ሊያልፈን አይገባም፡፡

#ዛሬም_ከተለዋዋጭ_ማንነት_እንጠበቅ፡፡

#ሰው_እንጂ_አካባቢውን_የምንመስል_እስስት_አይደለንም፡፡

ጌታ ሆይ እውነተኛ ፍቅርን እንዳንገፋ እባክህን እርዳን፡፡ "

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ
መልካም ምሽት

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →