የምስጋና መልእክት
ለአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እና ለአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች
ተማሪ አብራክ ነዋይ የልብ ቀዶ ህክምናውን በሰላም አጠናቆ ነገ ማለትም 4/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት በአርባምንጭ ይደርሳል የሚለውን አስደሳች ዜና በታላቅ ደስታ እናካፍላለን።
በዚህ አስቸጋሪ የህክምና ጊዜ ውስጥ ከጎኑ በመቆም በገንዘብ፣ በሞራል፣ በጸሎት እና በተለያዩ ድጋፎች የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በተለይም፦
ለትምህርት ቤቱ ውድ ጓደኞቹ፣
ለክቡራን መምህራን፣
እንዲሁም ለመላው የአርባምንጭ ከተማ ማህበረሰብ፣
ያሳያችሁት ፍቅር፣ አንድነት፣ ርህራሄ እና ሰብአዊነት በእጅጉ የሚደነቅ ነው። ድጋፋችሁ የአንድ ተማሪ ህይወት እንዲታደግ ብቻ ሳይሆን ተስፋ እና ደስታን ለቤተሰቡ እና ለማህበረሰቡ ሁሉ አበርክቷል።
“እግዚአብሔር የሰጣችሁትን ቸርነት አብዝቶ ይክፈላችሁ፤ የልባችሁንም መልካም ፍላጎት ይባርክ።”
ተማሪ አብራክ ነዋይ ወደ ከተማችን በሰላም ሲመለስ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን፤ ለወደፊት ትምህርቱን እና ህይወቱን በጤና፣ በሰላም እና በስኬት እንዲቀጥል ከልብ እንመኛለን።
ከልብ እናመሰግናለን!
Post #319
365