ማስታወቂያ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተመዝግባችሁ መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ
ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ባቋቋማቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማር ሂደቱን እያከናወነ ይገኛል።
ሚኒስቴሩ በትምህርት ቤቶቹ የሚገኙ ተጨማሪ ክፍት ቦታዎችን በመጠቀም ተጨማሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የምዝገባ ዕድል አመቻችቷል።
በመሆኑም በትምህርት ቤቶቹ ባሉ ክፍት ቦታዎች ተመድባችሁ ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች ከታች በተጠቀሰው የምዝገባ ሊንክ በመግባት እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።
የምዝገባ ጊዜ፦ ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት
የምዝገባ ሊንክ፦ https://sbs.moe.gov.et/apply
የትምህርት ሚኒስቴር
Post #378
40
Forwarded from Ministry of Education Ethiopia
