TGViewer
ARBAMINCH UNIVERSITY COMMUNITY PRIMARY SCHOOL GRADE 6 ARBAMINCH UNIVERSITY COMMUNITY PRIMARY SCHOOL GRADE 6 @a1670 · 275 subscribers
Post #235 947
ፅኑ ስብዕና (resilient personality)

የወርቅ ንፅህና በእሳት ተፈትኖ እንደሚለየው የሰው ልጅ ፅናትም በመከራ ውስጥ ነው ፍንትው ብሎ የሚወጣው። ለምሳሌ ሁለት ነጋዴዎች በተመሳሳይ ጊዜ ሊከስሩ ይችላሉ። ማንነታቸው ግን የሚወሰነው በደረሰባቸው ኪሳራ ሳይሆን ለኪሳራው በሰጡት ምላሽ ይሆናል። አንዱ ተስፋ ቆርጦ ድባቴ ውስጥ ሊዘፈቅ ይችላል፣ ሌላው ደግሞ የተሻለ ለመስራት ሊነሳሳ ይችላል።

ለችግሩ እጅ የሰጠው የመጀመሪያው ሰው ደካማ የፅናት ስብዕና ያላቸው ሰዎች ምሳሌ ሲሆን፣ በችግሩ ያልተበገረው ሁለተኛው ሰው ግን የፅኑ ሰብዕና አይነተኛ ምሳሌ ተደርጎ ሊወሳ የሚችል ነው።

በዚህች አጭር ፅሁፍ የፅኑ ሰብዕና ምንነትና ጥቅሞች እንመለከታለን።

ፅኑ ስብዕና ምንድን ነው?

ፅኑ ስብዕና ማለት በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ተፈትኖ ማለፍ፣ ወድቆ የመነሳትና ችግሮችን ወደ ዕድል የመለወጥ ማንነት ነው። ለመሆኑ፣ የሰብዕናችን የፅናት ደረጃ ከፍ ያለ ወይ ዝቅ ያለ መሆኑን እንዴት እንለያያለን? ቀጥሎ 6 ነጥቦችን እንይ፦

ሀ) ቀና አመለካከት (Optimism)

ለነገሮች ያላቸው አመለካከት ቀና ነው። ሁሌም ችግሮች ጊዜአዊ እንደሆኑና "ሁሉ ነገር ለበጎ ነው" የሚል አስተሳሰብ አላቸው።

ለ) ተጣጣፊነት (flexibility)

በታላቅ አውሎነፋስ ውስጥ ብዙ ዛፎች ተገንድሰው ሲወድቁ የዘንባባ ዛፍ 🌴ግን ያንን አውሎ ንፋስ ዝቅ ብሎ ያሳልፍና መልሶ ቀና ይላል። ፅኑ ስብዕና ያላቸው ሰዎችም ልክ እንደ ዘንባባ ለተለያዩ ችግሮች የተለያዩ ምላሾች በመስጠት ያልፉታል፤ መናገር ሲገባቸው ይናገራሉ፣ ዝም ማለት ሲኖርባቸው አያወሩም፣ አንድን ችግር ችክ ብለው በተመሳሳይ መንገድ ለመፍታት አይዳክሩም።

ሐ) አለማስመሰል (Genuine)

ፅኑ ሰዎች ያልሆኑትን መስለው መታየት አይፈልጉም፤ ደካማ ጎናቸውን ለመሸፋፈን አይሯሯጡም። የሌላቸውን "አለኝ" ለማለት ለታይታ ሲሉ የተለያዩ ጭምብሎችን በማጥለቅና በማውለቅ አሳራቸውን አይበሉም።

መ) ተማሪነት

ለመንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ስኬትም ውድቀትም፣ ማጣትም ማግኘትም፣ ከፍታም ዝቅታም አንዳች ትምህርት ጥሎ ከማለፍ ውጪ አንዳች ጠባሳ አይተውባቸውም።

ረ) በሚቆጣጠሯቸው ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ

የፀና ሰብዕና ያላቸው ሰዎች ማድረግ በሚችሉት ጉዳይ ላይ እንጂ ከእነርሱ ቁጥጥር ውጭ ባለ ነገር ላይ አቅማቸውን አይጨርሱም።

ሰ) ጠንካራ ማሕበራዊ ቁርኝት

ፅኑ ሰብዕና ያላቸው ሰዎች ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ያላቸው እንጂ ብቸኞች አይደሉም።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፅኑ ሰብእና ያላቸው ሰዎች ከሌላቸው አንፃር ሲታዩ ሲበዛ ስኬታማና የተሻለ የአዕምሮና የአካል ጤንነት ያላቸው ናቸው።

ስለዚህ፣ ሁላችንም አይናችንን ከሚገጥሙን ተግዳሮቶች ላይ አንስተን የመውጫ መንገዶችን ብንመለከት፣ ከማለቃቀስ ይልቅ የማንቀይረውን ብንቀበልና በሁሉ ብንደሰት የስኬት መንገድ ላይ መሆናችን አያጠያይቅም።
(ሳይኮሎጂ 101)
  • 👍 4
  • ❤ 3
More from @a1670
  1. Oct 11, 20261. መማር ተግባር ነው። ትምህርትን ለማግኘት መጀመር፣ መጣርና በተግባር መለማመድ ያስፈልጋል። 2. የተማርነውን ማስቀጠል ልማድ ነው። በየቀኑ…
  2. Oct 9, 2026ማስታወቂያ በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተመዝግባችሁ መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ባቋቋማቸው…
  3. Oct 8, 2026ነገ ወደ ጋሞ ባይራ አዳሪ ትምህርት ቤት በመግባት አዲስ የትምህርት ምዕራፍ ትጀምራላችሁ። ይህ አዲስ ጉዞ በእውቀት፣ በስኬት፣ በጥሩ ሥነ-ምግባ…
  4. Oct 6, 2026🌿 ለውድ ተማሪዎቼ 🌿 ከዚህ በፊት በትጋት፣ በጽናትና በትምህርት ያሳያችሁት አበረታች አፈጻጸም ዛሬ ወደ አዲስ የትምህርት ምዕራፍ እንድትሸጋ…
  5. Oct 6, 20261. Adonis Akililu Alemayehu 2. Amesias Bogale G/Mariam 3. Amir Seid Mohammed 4. Eleni Meko…
  6. Sep 29, 2026የጋሞ ባይራ ትምህርት ቤት መግቢያ ቀን እስኪገለፅ ድረስ ትምህርታችሁን መጥታችሁ መከታተል ትችላላችሁ ።
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →