TGViewer
Polymorphism🌗 Polymorphism🌗 @inpolymorphism · 53 subscribers
Post #273 146
ከቶ አይቀርም ሞቱ
ምንም ቢታክቱ ምን ቢሰነብቱ
—
ሞት ፊደል ተምሮ ያነባል ስንል
እንኳን ሊያነብና ገና ያግዛል
—
እህል ታሟል አሉ በእግሬ ልገስግስ
እሞት የለሁም ወይ በቅሎማ እስኪደርስ
—
እኔን መስሎኝ ነበር ደሃ ነው ደካሚ
ለካስ ሁሉም ኖሯል አፈር ተሸካሚ
—
በሉ እናንተም ሂዱ እኛም ወደዚያው ነው
ወትሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው
—
ለሠሪው ለመስጠት አፈሩን ይዣለሁ
ገል አፈር መሆኑን ተረድቼዋለሁ
—
እኔስ ፍረድ ቢሉኝ ሞት በደለኛ ነው
አንድ ሰው ለምስል ቀምሶ ቢቀር ምነው
—
ሞት ይቅር ይላሉ ሞት ቢቀር አልወድም
ድንጋዩም አፈሩም ከሰው ፊት አይከብድም።
—
ሂያጅ ተሳፋሪ ሰዎች ከሆናችሁ
ኧረ ለመቼው ቀን ቤት ትሠራላችሁ።
—
እረገጡኝ ብለህ ምድር አትቆጣ
ይህ ሁሉ ያንተ ነው ሸማውን ቢያነጣ።

— መጋቤ ስብሃት ዓለሙ አጋ

@inPolymorphism🌓
  • ❤ 3
More from @inpolymorphism
  1. Sep 14, 2026በደከመ ፡ ጉልበት ፡ ባለኝ ፡ በሌለ ፡ አቅም ፥ ለአንድ ፡ ቀን ፡ ዘንግቼሽ ፡ ውዬ ፡ አድሬ ፡ አላውቅም። ❤️‍🩹 Ah.... 🎵ቴዲ @i…
  2. Sep 1, 2026Some people have found God in the depth of their sin, while some have lost him in the heig…
  3. Aug 30, 2026The deepest form of slavery is the hunger for being understood. 😊 — Fyodor Dostovsky @inP…
  4. Aug 29, 2026Some are born to enjoy illusions, others are cursed to see the truth. 😊 — Friedrich Nietz…
  5. Aug 21, 2026ለድህነቴ መልስ ፡ እጄን ሞላህልኝ ለሰባራው ስሜ ፡ ስምህን ሰጠኸኝ ሊቶስጥራን አልፈህ ፡ በመስቀል ጠራኽኝ ጎዶሎ አይደለሁም ፡ ባንተ ዘንድ ሙ…
  6. Jul 25, 2026There is nothing in this world that can trouble you as much as your own thoughts. 😊 @inPo…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →