ለድህነቴ መልስ ፡ እጄን ሞላህልኝ
ለሰባራው ስሜ ፡ ስምህን ሰጠኸኝ
ሊቶስጥራን አልፈህ ፡ በመስቀል ጠራኽኝ
ጎዶሎ አይደለሁም ፡ ባንተ ዘንድ ሙሉ ነኝ።
—
የምሰክርብህ ፡ ሰማያዊ ወይኔ
የፍካት ጸዳል ነህ፡ የዓይን ብርሃኔ
የምኮራብህ ፡ መመኪያ ወገኔ
ሌላ አምላክ የለኝም ፡ እንዳትለይ ከኔ
ሌላ ረዳት የለኝም ፡ እንዳትለይ ከኔ
ሌላ ንጉሥ የለኝም ፡ እንዳትለይ ከኔ
ሌላ አባት የለኝም ፡ እንዳትለይ ከኔ
ሌላ...
ሌላ...
☦️
@inPolymorphism🌓
Post #286
93
- ❤ 2