TGViewer
Channel ✦ Verified Channel
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/

Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/

@ethpress

Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Subscribers
24.8K
Photos
41.4K
Videos
346
Links
5.8K

Showing posts older than #46605 · Back to latest

Older Posts 6 shown
Post #46595 4.46K
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ኢትዮጵያን በመረጃ ላይ የተመሠረተ የልማት መጻኢ ዕድል የሚያሳየው ''በመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት'' ብሔራዊ ጉባኤ ላይ የቀረቡ የብሔራዊ ዕቅድና ስታቲስቲክስ ዳሽቦርዶች (የመረጃ መከታተያ ሰሌዳዎች) እና ኤግዚቢሽን ያደረጉት ጉብኝት። #PMOEthiopia
  • ❤ 4
  • 👍 3
Post #46593 2.49K
''የማዳበሪያ ፋብሪካው በሚጠናቀቅበት ወቅት የሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን ያጎለብታል፤ ጥገኝነት ይቀንሳል፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮቻችንን ይደግፋል። ለኢንቨስትመንትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ አዳዲስ ዕድሎችን ይከፍታል''

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

#ጋዜጣፕላስ #fertilizerindustry #productivity #ተኪምርት #gazetteplus #dangoterefinery #Dangote
  • ❤ 2
Post #46592 2.73K
በምግብ ራስን መቻል ዋነኛ አጀንዳችን ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
#dangotecement #fertilizerindustry #EthiopiaDelivers #productivity #ጋዜጣፕላስ
Post #46591 2.98K
የማዳበሪያ ፋብሪካው የምግብ ሉዓላዊነት፣ የኢንዱስትሪ እድገትና በኢኮኖሚ ራስ የመቻል ጥረት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ኢንቨስትመንት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - በኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ የምግብ ሉዓላዊነት፣ የኢንዱስትሪ እድገትና በኢኮኖሚ ራስ የመቻል ጥረት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ኢንቨስትመንት መሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንዳሰታወቁት፤ ባለፈው አመት ነሐሴ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመሆን በአመት 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካ ለማቋቋም ትልቅ የባለድርሻ ስምምነት አድርገን ነበር።

በያዝነው አመት ጥቅምት ወር ደግሞ የፕሮጀክቱን ግንባታ በይፋ ጀምረናል። ይኽ ሥራ ከመሠረተ ልማት ግንባታም በላይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ የምግብ ሉዓላዊነት፣ የኢንደስትሪ እድገት እና በኢኮኖሚ ራስ የመቻል ጥረት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ኢንቬስትመንት መሆኑን ገልጸዋል።

የማዳበሪያ ፋብሪካው በሚጠናቀቅበት ወቅት የሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን ያጎለብታል፣ ከውጭ በሚገባ ማዳበሪያ ላይ ያለውን ጥገኝነት ይቀንሳል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አርሶአደሮቻችንን ይደግፋል።

ለኢንቨስትመንትና የሥራ ዕድል ፈጠራም አዳዲስ እድሎችን ይከፍታል።

ዛሬ ማለዳ ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን በጎዴ ተገኝቼ ሥራው የደረሰበትን ደረጃ ለመገምገም የፕሮጀክት ስፍራውን ጎብኝቻለሁ። በመላው የፕሮጀክቱ ስፍራ የሚታየው የሥራ ሂደቱ ፍጥነት አበረታች ነው።

ይኽን ግዙፍ እና እጅግ ጠቃሚ ሀገራዊ ፕሮጀክት ለመፈፀም ያለውን ቁርጠኝነት እና ትብብር በሚያንፀባርቅ ሁኔታ በተለያዩ የፕሮጀክቱ ክፍሎች ያሉት ግንባታዎች በእቅዳችን መሠረት እየተጓዙ ይገኛሉም ብለዋል።

#ግብዓትአቅርቦት #PMOEthiopia #DigitalTransformation #FinancialFreedom #fertilizerindustry
  • ❤ 3
Older posts →
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →