Post #46554
2.91K

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 'ኢትዮጵያ ታምርት' ኤክስፖ 2018 በይፋ መርቀው ከፈቱ
+++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የአምራች ዘርፍ ለማስፋፋት የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክረውን አራተኛውን 'ኢትዮጵያ ታምርት' ኤክስፖ 2018 ዛሬ በይፋ መርቀው ከፍተዋል።
ኤክስፖው እስካሁን ያሳያቸውና የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች
✍️ የአምራች ዘርፉ ግብዓት አቅርቦት በዓመት ከ9 ሚሊዮን ወደ 15 ሚሊዮን ቶን አድጓል፤
✍️ ለአዳዲስ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች ከ3.4 ጊጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ቀርቧል፤
✍️ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርበው የፋይናንስ አቅርቦት ከ8.1 ቢሊዮን ወደ 50 ቢሊዮን ብርአድጓል፣
✍️ ለከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ከ262 ቢሊዮን ብር በላይ ከፍ ብሏል፤
✍️ ለዘርፉ ከ2.28 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተመድቧል፤
✍️ የፋብሪካዎች የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ አድጓል፤
✍️ የማምረት አቅምና ዕድገት ከ4.8 በመቶ ወደ 10.7 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን፣ በቀጣይም ተጨማሪ ዕድገት ይጠበቃል፤
✍️ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት እስከ 4.85 ቢሊዮን ዶላር ማዳን የተቻለ ሲሆን የወጪ ንግድም አድጓል፣
✍️ ከ2,800 በላይ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ የተቻለ ሲሆን፣ ለ1.4 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።
ኤክስፖው ኢንዱስትሪዎችን የሚያስተሳስር፣ ኢንቨስትመንትን የሚስብ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ አምራቾችንና ጎብኚዎችን የሚያገናኝ ቁልፍ ሀገራዊ መድረክ ሆኗል። የኤክስፖው ለዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ያለውን ፋይዳ በማጉላት የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ሽግግር እያፋጠነ መሆኑን ያሳያል። #PMOEthiopia #EthiopiaDelivers

- ❤ 7