TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46554 2.91K
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 'ኢትዮጵያ ታምርት' ኤክስፖ 2018 በይፋ መርቀው ከፈቱ
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የአምራች ዘርፍ ለማስፋፋት የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክረውን አራተኛውን 'ኢትዮጵያ ታምርት' ኤክስፖ 2018 ዛሬ በይፋ መርቀው ከፍተዋል።
‎
‎ኤክስፖው እስካሁን ያሳያቸውና የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች

✍️ የአምራች ዘርፉ ግብዓት አቅርቦት በዓመት ከ9 ሚሊዮን ወደ 15 ሚሊዮን ቶን አድጓል፤

‎✍️ ለአዳዲስ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች ከ3.4 ጊጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ቀርቧል፤

‎✍️ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርበው የፋይናንስ አቅርቦት ከ8.1 ቢሊዮን ወደ 50 ቢሊዮን ብርአድጓል፣

✍️ ለከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ከ262 ቢሊዮን ብር በላይ ከፍ ብሏል፤

‎✍️ ለዘርፉ ከ2.28 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተመድቧል፤

‎✍️ የፋብሪካዎች የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ አድጓል፤

‎✍️ የማምረት አቅምና ዕድገት ከ4.8 በመቶ ወደ 10.7 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን፣ በቀጣይም ተጨማሪ ዕድገት ይጠበቃል፤

‎✍️ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት እስከ 4.85 ቢሊዮን ዶላር ማዳን የተቻለ ሲሆን የወጪ ንግድም አድጓል፣

‎✍️ ከ2,800 በላይ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ የተቻለ ሲሆን፣ ለ1.4 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።
‎
‎ኤክስፖው ኢንዱስትሪዎችን የሚያስተሳስር፣ ኢንቨስትመንትን የሚስብ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ አምራቾችንና ጎብኚዎችን የሚያገናኝ ቁልፍ ሀገራዊ መድረክ ሆኗል። ‎የኤክስፖው ለዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ያለውን ፋይዳ በማጉላት የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ሽግግር እያፋጠነ መሆኑን ያሳያል። #PMOEthiopia #EthiopiaDelivers
  • ❤ 7
More from @ethpress
  1. Oct 10, 2026በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም ያለው የማጣሪያ ፋብሪካ ስራ ጀመረ +++++++++++++++ #ጋዜጣ ፕላስ-በኢትዮጵያ…
  2. Oct 8, 2026የመደመር መንግስት አዲሱ ካቢኔ #የመደመር_መንግሥት #PMOEthiopia #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
  3. Oct 8, 2026አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣…
  4. Oct 8, 2026ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን የሚኒስትሮች ሹመት አፀደቀ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የሕዝብ ተወካዮ…
  5. Oct 6, 2026በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከል እንዲገቡ ጥሪ ቀረበ ++++++++++++++ #ጋዜት_ፕላስ- በትግራይ ክልል ሲ…
  6. Oct 6, 2026photo post
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →