Post #46171
1.84K “የነበረው ጭቅጭቅ ይታወሳል፤ ነገር ግን ሰላም ነው ሚሻለው ብለን የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ ከፍለናል”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር በትግርኛ ባደረጉት ቆይታ
#PMOEthiopia
Post #46169
1.98K “አፍሪካውያን ጂኦ-ፖለቲካዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር ከዓድዋ ሊማሩ ይገባል”
- ፓን አፍሪካኒስቶች
+++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | አፍሪካውያን ጂኦ-ፖለቲካዊ ጥቅማቸውንና ሉዓላዊነታቸውን ለማስከበር የዓድዋን የአንድነትና የእኩልነት እሳቤ ሊቀስሙ እንደሚገባ የፓን አፍሪካኒስት ባለሙያዎች ገለጹ።
ባለሙያዎቹ ይህንን የገለጹት 130ኛው የዓድዋ ድል በዓል በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት እየተከበረ በሚገኝበት ወቅት ሲሆን፤ የአፍሪካ ሕዝቦች የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤን ማጎልበት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
ፓን አፍሪካኒስት ሕይወት አዳነ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ዓድዋ ያለ አንድነትና ትብብር ድል እንደሌለ በተግባር ያሳየና የውጭ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም ሥነ-ልቦናዊ ጫናዎችን ለመቋቋም ያስቻለ ታላቅ ድል ነው።
በአሁኑ ወቅት የምዕራቡ ዓለም ርዕዮተ ዓለምና የኃያላን ፉክክር በአፍሪካ ላይ ጫና እያስከተለ መሆኑን ጠቁመዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካና ኤዥያ ጥናት ተመራማሪ ዳዊት መዝገበጸጋዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በምዕራባውያን ተቋማትና መንግሥታት የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስና የቀጠናውን ጥቅም ለማስከበር ዓድዋ ዋነኛው መንገድ መሆኑን ገልጸዋል።
የአፍሪካ መሪዎችና አህጉራዊ ተቋማት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የወታደራዊ ጥንካሬን ለመገንባት በአንድነት ሊሠሩ እንደሚገባ መክረዋል።
ዓለም አቀፋዊ ጫናዎችን ለመቋቋም አፍሪካውያን በዓድዋ የአንድነት መንፈስ በመመራት የጋራ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ በጋራ መቆም እንዳለባቸውም ባለሙያዎቹ በአጽንኦት አሳስበዋል።
በልጅዓለም ፍቅሬ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ዓድዋ #ፓን_አፍሪካኒዝም #አፍሪካ #ጂኦ_ፖለቲካ #ሉዓላዊነት #ሕይወት_አዳነ #ዳዊት_መዝገበጸጋዬ
Post #46168
2.65K የባሕር በር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ማድረግ የዘመናችን ዓድዋ ነው
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ማድረግና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የዘመናችን የዓድዋ ድል ተደርጎ የሚቆጠር መሆኑን የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ሰለሞን ተፈራ ገለጹ።
ምሁሩ ሰለሞን ተፈራ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ የዓድዋ ድል የሀገሪቱን የግዛት ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተደረገ ታላቅ ተጋድሎ እንደነበረ ሁሉ፣ እውነተኛ ሉዓላዊነት የሚረጋገጠው ደግሞ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ነፃነት ማረጋገጥ ሲቻል ነው።
የባሕር በር ማጣት ኢትዮጵያን የጂኦግራፊ እስረኛ በማድረግ የኢኮኖሚ ነፃነቷን እንደሚገድብ የጠቀሱት ምሁሩ፣ ይህንን ጥያቄ መፍታት የዘመናችን የዓድዋ ድል ተደርጎ እንደሚወሰድ አስረድተዋል።
እንደ ሰለሞን ማብራሪያ፤ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በዓድዋ መንፈስና በአንድነት በመቆማችን የተመዘገበ ሁለተኛው የዓድዋ ድል ነው።
በተመሳሳይ የባሕር በር ጉዳይም መላው ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመው ሊያሳኩት የሚገባ ብሔራዊ አጀንዳ መሆኑን ጠቁመዋል።
አየር መንገድ ያስጀመረው አዲስ አየር ማረፊያ እና የኒውክሌር ኃይል ግንባታ ጥረቶችም የአባቶቻችንን የፖለቲካ ድል በኢኮኖሚ በማጀብ የሀገርን ክብር የሚያጸኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መሆናቸውን አመልክተዋል።
በፋንታነሽ ክንዴ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ዓድዋ_ድል #ኢትዮጵያ #የባሕር_በር #ሉዓላዊነት #ኢኮኖሚ #ሰለሞን_ተፈራ
Post #46167
2.44K “ኢትዮጵያ የባሕር በር አያስፈልጋትም የሚል የፖለቲካ ፓርቲ ካለ መሰረዝ ነው ያለበት”
- አቶ ግርማ ሰይፉ
+++++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ኢትዮጵያ የባሕር በር አያስፈልጋትም የሚል የፖለቲካ ፓርቲ ካለ ከፓርቲነት ተሰርዞ ከፖለቲካው ምዕራፍ መውጣት እንዳለበት የኢዜማ አመራርና የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ግርማ ሰይፉ ተናገሩ።
አቶ ግርማ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ የሀገሪቱን የባሕር በር የማረጋገጥ ጉዳይ በቀጣይ ሕገ-መንግሥቱ በሚሻሻልበት ወቅት ትኩረት ተሰጥቶት የመንግሥት ግዴታ ተደርጎ ሊደነገግ ይገባል።
ለዚህም እንደ ምሳሌ ያነሱት የግብፅ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 19 የናይልን ውኃ ደኅንነት ማስጠበቅ የመንግሥት ግዴታ መሆኑን እንደሚደነግግ ጠቅሰው፣ በኢትዮጵያም የባሕር በርን ማስጠበቅ ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
ብሔራዊ ጥቅምን የማስከበር ኃላፊነት በመንግሥት ላይ መጣል እንዳለበት የገለጹት አቶ ግርማ፤ ከዚህ ብሔራዊ ጥቅም በተቃራኒ የሚቆሙ አካላትን መቆጣጠር የመንግሥት ግዴታ ሊሆን እንደሚገባም አመልክተዋል።
የባሕር በር ጥያቄ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ባለፈ የሀገር ህልውና ጉዳይ መሆኑንና ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ለዚህ ግብ መሳካት ቅድሚያ መስጠት እንዳለበትም በአጽንኦት ገልጸዋል።
በማህሌት አብዱል
#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #የባሕር_በር #ብሔራዊ_ጥቅም #ፖለቲካ_ፓርቲ #ግርማ_ሰይፉ #ሕገ_መንግሥት
Post #46165
2.85K ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር በትግርኛ ያደረጉት ቆይታ- ነገ ምሽት 2:30 ይጠብቁን!
ቀዳማይ ሚኒስትር ዐቢይ ኣሕመድ(ዶ/ር) ምስ ኢዜኣ ብቋንቋ ትግርኛ ዝገበርዎ ፃንሒት- ፅባሕ ምሸት ሰዓት 2፡30 ይፀበዩና!
#PMOEthiopia
Post #46159
2.75K ዛሬ ምሽት እንደተለመደው በረመዳን መንፈስ ከቡሩንዲ፣ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ከሶማሊያ፣ ከኢራቅ፣ ከሶሪያ፣ ከፍልስጤም፣ ከአፍጋኒስታን፣ ከኤርትራ፣ ከየመንና ሱዳን ከመጡ ስደተኞች ጋር አፍጥር ታድመናል።
-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)