TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46780 4.6K
የአፍሪካ ተወካዮች ስለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ...
++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - በይፋ የተጀመረው ታሪካዊው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በርካታ አህጉራዊና ዓለም አቀፋ እንግዶች የተገኙበት የአፍሪካ ተወካዮች ስለሀገራዊ ምክክሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክቶቻቸውም ሀገራዊ ምክክሩ "በኢትዮጵያውያን የተመራና የኢትዮጵያውያን የሆነ"፣ የአፍሪካ ኅብረትን "አጀንዳ 2063" ራዕይ የሚያሳካና የአፍሪካውያንን ችግር በአፍሪካውያን የመፍታት መርህን በተግባር ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።

✅ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልክተኛ ቺፍ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ

የኢትዮጵያን ታሪክ፣ የህዝቦቿን ብዝሃነትና ታታሪነት በመጥቀስ ይህ ህዝብ የሰነቀውን ብሩህ ተስፋ ለማሳካት ደግሞ አሁን የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ስኬት ቁልፍ መሆኑን ተናግረዋል።

✅ የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ በሀገራዊ ምክክር መክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት

በዓለም ታሪክ ውስጥ በግጭት የተገነባ ወይም ያተረፈ ሀገር የለም። በፖለቲካ ባህል ውስጥ ልዩነቶች መኖራቸው ተፈጥሮአዊ ቢሆንም፤ ትልቁና መሰረታዊው ስህተት ግን እነዚህን ልዩነቶች በኃይል ለመፍታት መሞከር ነው። ከሁሉ በላይ ልዩነቶችን መፍታት የሚቻለው በሰላማዊ መንገድ፣ በመነጋገርና በተለያዩ ሰላማዊ መድረኮች መሆኑን ይገባል። ኢትዮጵያም ለዚህ የሚሆኑ በርካታ ባህላዊ የምክክር መንገዶች ያሏት ሀገር መሆኗን ጠቅሰዋል።

✅ የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ፣ የሰላም እና የደህንነት ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ

በዚህ ታሪካዊ ስፍራ ተገኝተው የዚህ ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ አካል መሆን ለአፍሪካ ህብረት ትልቅ ኩራት መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ የሂደቱንም ታላቅነት፣ ስፋትና ጥንካሬ በከፍተኛ ሁኔታ አድንቀዋል። የአፍሪካ ህብረት ይህንን ታሪካዊ ክስተት በሙሉ አቅሙ እንደሚደግፍ በማረጋገጥ፣ ይህ የጋራ ጉዞ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን፣ ልማትንና አዎንታዊ ለውጥን ማምጣት እንደምትችል የሚያሳይ ህያው ምስክር መሆኑን አመላክተዋል።

ኢትዮጵያ የገጠማትን ውስብስብ የፖለቲካ ችግር መፍታት የምትችለው የራሷን ጥንታዊ የዕርቅ እሴቶች በመጠቀምና ሁሉንም አሳታፊ ያደረገ ፖለቲካዊ መፍትሄ በማምጣት ብቻ መሆኑን ነው። ለዚህ ታሪካዊ ሽግግር ዋነኛው መሻጋሪያ ድልድይ መሆኑና ለአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ እንደሚሆን በመልዕክታቸው ገልጸዋል።

#Ethiopia #AfricanUnion #IGAD #PeaceBuilding #Agenda2063 #AfricanSolutions
  • ❤ 3
More from @ethpress
  1. Oct 3, 2026photo post
  2. Oct 2, 2026Irreechi Nagaadha! Gadaan Qaroomina! Qaroominni Itoophiyaa hin oolleedha! Baga bacaqii gan…
  3. Oct 2, 2026ኦርዲን በድሪ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሰየሙ #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
  4. Oct 1, 2026ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋ እንዲዘጋ ወሰነች ++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን እንዲዘጋ…
  5. Oct 1, 2026አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሰየሙ ++++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የሶማሌ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ…
  6. Oct 1, 2026#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ እንደምን አደራችሁ - #አዲስ_ዘመን_ጋዜጣ- https://press.et/e-paper
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →