ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋ እንዲዘጋ ወሰነች
++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን እንዲዘጋ መወሰኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የኢትዮጵያ መንግሥት 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታ ከኢትዮጵያ እንዲወጡም ወስኗል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በቪየና የዲፕሎማሲ ስምምነትን ጥሰዋል የተባሉ አስር ኤርትራውያን ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ኢትዮጵያን እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥቷዋል።
ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸመችው ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ የጠብ አጫሪነት እና የትንኮሳ ድርጊቶች ምላሽ ለመስጠት በአስመራ፣ ኤርትራ የሚገኘውን ኤምባሲውን ለመዝጋት መወሰኑን የሚኒስቴሩ መግለጫ ያመለክታል።
Post #46940
1.68K

- ❤ 1
- 👍 1
- 👎 1