ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኳታር መንግሥትና ሕዝብ የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ
++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀድሞው የኳታር አሚር ሼክ ሐማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ በማረፋቸው የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ፤ በራሳቸው፣ በመንግሥትና በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ለኳታሩ አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሐማድ አል ታኒ፣ ለሀገሪቱ መንግሥትና ለወንድም የኳታር ሕዝብ ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ከመጀመሪያው ሒጅራ ጀምሮ የቆየ ታሪካዊ መሠረት እንዳለው ይገልጹ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰው የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት በአሁኑ አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሐማድ አል ታኒ መሪነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። በሞት ለተለዩት መሪ ዕረፍትን፣ ለቤተሰቦቻቸውና ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል።
Post #46777
4.83K

- 👍 6
- ❤ 2
- 👎 2