TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46755 2.74K
በአዲስ አበባ 543 ትምህርት ቤቶች የ6ኛ ክፍል ፈተና ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ ችለዋል- የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ ⵏበከተማው የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ 768 ትምህርት ቤቶች መካከል 543 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳለፍ መቻላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት 50 በመቶ እንዲሆን ወስኗል።

የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ፤ ፈተናውን ከወሰዱት ከ97 በመቶ በላይ የሚሆኑት ወደ ቀጣይ ክፍል ተዘዋውረዋል። 543 ትምህርት ቤቶችም የ6ኛ ክፍል ፈተና ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ ችለዋል።

የማለፊያ ነጥብ ለመደበኛ ተማሪዎች 50 በመቶ እንዲሁም 45 በመቶ ለአካል ጉዳተኞች መወሰኑን ተናግረዋል።

በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በቀንና በማታ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ከ85 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጸው፤ በዘንድሮው ፈተና ሁለት ተማሪዎች 98 አማካይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ጠቁመዋል።

459 ተማሪዎች 95 እና ከዚያ በላይ አማካይ ማስመዝገባቸውን ጠቅሰው፤አምስት ሺህ 559 የሚሆኑት ከ90 በላይ አማካይ ያስመዘገቡ ናቸው ብለዋል።

አጠቃላይ ውጤቱ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በሁለት ነጥብ አራት በመቶ እድገት ማሳየቱንም ገልጸው፣ ከዛሬ ጀምሮ ተማሪዎች ውጤታቸውን በኦላይን መመልከት የሚችሉ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

በልጅዓለም ፍቅሬ
+++++++++++++++++
#Gazetteplus #ጋዜጣፕላስ #AddisAbaba #AddisAbabaEducation #Grade6Exam
  • 👍 3
More from @ethpress
  1. Oct 4, 2026"የዘንድሮው የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በስኬት ተጠናቅቋል" - የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ +++++++++++ #ጋዜጣ_…
  2. Oct 4, 2026ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ #ጋዜጣ_ፕላስ #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
  3. Oct 3, 2026https://youtu.be/oXi2-SwdwbY
  4. Oct 3, 2026የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የተገኙና የአጀንዳ ነጥቦች እና ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ም…
  5. Oct 3, 2026photo post
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →