TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46731 2.43K
"ኩሪፍቱ የግሉ ዘርፍ ማበርከት የሚችለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በግልጽ የሚያሳይ ነው"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ የመደመር መንግሥት የገነባቸውን መሠረተ-ልማቶች ተከትሎ የግሉ ዘርፍ ማበርከት የሚችለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በግልጽ የሚያሳይ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

‎በአርባ ምንጭ ከተማ በ52,000 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈውን የኩሪፍቱ ሪዞርትና ስፓ ዛሬ ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አርባ ምንጭ፤ የልማት ምንጭነቷ እየጎመራ ቀጥሏል! ብለዋል።
‎
‎ይህ ታላቅ ፕሮጀክት 53 ቅንጡ ቪላዎችን ያካተተ ሲሆን፣ ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሰል ኢንቨስትመንቶች የመደመር መንግሥት የገነባቸውን መሠረተ-ልማቶች ተከትሎ የግሉ ዘርፍ ማበርከት የሚችለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በግልጽ የሚያሳይ ነው ብለዋል።
‎
‎የሀገራችንን የቱሪዝም አቅም ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ መሰል ታላላቅ ፕሮጀክቶች ላይ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች በስፋት እንዲሰማሩና መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።
#EthiopiaDelivers #InvestInEthiopia
  • ❤ 2
More from @ethpress
  1. Oct 4, 2026photo post
  2. Oct 4, 2026"የዘንድሮው የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በስኬት ተጠናቅቋል" - የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ +++++++++++ #ጋዜጣ_…
  3. Oct 4, 2026ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ #ጋዜጣ_ፕላስ #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
  4. Oct 3, 2026https://youtu.be/oXi2-SwdwbY
  5. Oct 3, 2026የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የተገኙና የአጀንዳ ነጥቦች እና ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ም…
  6. Oct 3, 2026photo post
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →