TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46521 2.9K
ከ800 በላይ የቱሪስት መስህቦች ተለይተዋል
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በኢትዮጵያ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን ለመለየትና ለመመዝገብ በተከናወኑ ስራዎች እስካሁን ከ800 በላይ የመስህብ ቦታዎች በሦስት ደረጃዎች ተለይተው መመዝገባቸውን የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሯ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ፣ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙና እስካሁን ያልታወቁ የቱሪስት መስህቦችን የመለየትና የመመዝገብ ሥራ በበጀት ዓመቱ በስፋት ሲከናወን ቆይቷል።

በዚህም እስካሁን ከ800 በላይ የመስህብ ቦታዎችን በመለየት በሦስት ደረጃዎች መድቦ ማስቀመጥ መቻሉን ጠቁመው፤ እነዚህ ደረጃዎች የተለዩት የመስህቦቹ የመልማት አቅም፣ ከየአካባቢው ያላቸው ተደራሽነትና ሊሠራባቸው በሚችሉ ዝርዝር መስፈርቶች መሠረት መሆኑን አስረድተዋል።

የተለዩ ሀብቶች በትንሽ የኢንቨስትመንት ድጋፍ መልማት የሚችሉ መሆናቸውን የጠቀሱት ሚኒስትሯ፤ የመስህቦቹን መገኛና ዝርዝር ሁኔታ ማወቅ ለዘርፉ ልማት መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑንም አመላክተዋል።

ለዚህ የልማት ተግባር ስኬታማነት ከፌዴራልና ከክልል መንግሥታት እንዲሁም ከሕዝቡ የሚጠበቀውን ድርሻ የማስተባበር ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በሀገሪቱ ያሉ የቱሪስት መስህቦች 800 ብቻ እንዳልሆኑ የገለጹት ሰላማዊት ካሳ፤ አሁን የተከናወነው የመለየት ሥራ የመጀመሪያ ዙር መሆኑንና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እነዚህን ሀብቶች በማልማትና ለቱሪዝም ክፍት በማድረግ ረገድ በቀጣይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ አስገንዝበዋል።
  • ❤ 8
  • 😁 2
  • 👍 1
More from @ethpress
  1. Oct 10, 2026በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም ያለው የማጣሪያ ፋብሪካ ስራ ጀመረ +++++++++++++++ #ጋዜጣ ፕላስ-በኢትዮጵያ…
  2. Oct 8, 2026የመደመር መንግስት አዲሱ ካቢኔ #የመደመር_መንግሥት #PMOEthiopia #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
  3. Oct 8, 2026አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣…
  4. Oct 8, 2026ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን የሚኒስትሮች ሹመት አፀደቀ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የሕዝብ ተወካዮ…
  5. Oct 6, 2026በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከል እንዲገቡ ጥሪ ቀረበ ++++++++++++++ #ጋዜት_ፕላስ- በትግራይ ክልል ሲ…
  6. Oct 6, 2026photo post
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →