የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ - በባህልና ስፖርት ዘርፍ - የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ
ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት የባህልበ ስፖርት ዘርፍ የተመዘገቡ ዓበይት ስኬቶች ቀርበዋል።
የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ በሚል የተዘጋጀውና በማህበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የሚቀርቡበት የምክክር መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።
የባህል እና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካ፤ ከለውጡ በፊት ዘርፉ ከነበሩበት ክፍተቶች መካከል፤ ለአደባባይ ክብረ በዓላት ትኩረት ማነስ፣ ባህላዊ የፍትህና ዳኝነት ስርዓትን ያለመጠቀም፣ የአካታችነት ችግር እንዲሁም የባህል እሴቶችን ለአንድነት ያለመጠቀም ከብዙ ጥቂቶች ናቸው።
የለውጡ መንግሥት ለነዚህ ክፍተቶች ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ዘርፉ ወሳኝ ለውጦች እንዲያስመዘግብ መደላድል ፈጥሯል። ከስኬቶቹም፤ ለ83 ክብረ በዓላት እውቅና መስጠትና መከበር፣ 36 አዲስ ባህል ማዕከላት መገንባት፣ ዲጂታል የቅርስ መረጃ አያያዝ ስርዓት መዘርጋት፣ የባህልና የብዝኃ ልሳን ፖሊሲ ትግበራ፣ ተጨማሪ ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኙ የማይዳሰሱ የባህል ቅርሶች፣ በርካታ ቤተ-መጻሃፍት ግንባታና የንባብ አገልግሎት መበራከት፣ ብዝሃ ልሳን ፖሊሲ ትግበራና የሙያ ማህበራት መደራጀት እንዲሁም ዘርፉን ለዲፕሎማሲ ስኬት ከመጠቀም ባለፈ አደይ አበባን ጨምሮ 17,636 አዳዲስ ስታዲየሞች ግንባታ የዘርፉ ትልቅ እመርታዎች ናችው። #PMOEthiopia
Post #46519
2.01K

- ❤ 2