TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46415 2.73K
“የትግራይ ወጣት ከአሁን በኋላ በጦርነት ማለቅ የለበትም”

- ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም
++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የትግራይ ወጣት ከአሁን በኋላ በጦርነት ሕይወቱን ማጣት እንደሌለበትና ማንኛውም የሕዝቡ ጥያቄ በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ብቻ መፈታት እንዳለበት የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም (ወ/ሮ) አሳሰቡ።

የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም ከጋዜጣ ፕላስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳብራሩት፤ “አንድም የትግራይ ወጣት ደም መፍሰስ የለበትም፤ አሁን ጦርነት አያስፈልገንም።”

ወጣቱ ከአሁን በኋላ ደም መክፈል እንደሌለበት የገለጹት ዋና አፈ ጉባኤዋ፤ የትግራይ ሕዝብ ጥያቄዎች በጦርነት ሳይሆን በውይይት መፈታት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የትግራይ ወጣት “ከአሁን በኋላ ጦርነት በቃን፤ መኖር እንፈልጋለን፤ ጥያቄ ካለም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንወያይበታለን” የሚል ግልጽ መልዕክት እያስተላለፈ መሆኑን ጠቁመዋል።

አሁን የሚያስፈልገው ቁጭ ብሎ በጠረጴዛ ዙሪያ ችግሮችን መፍታት መሆኑንም አክለዋል። ወጣቱ የትግራይ ሕዝብ ጥያቄ በመመካከርና በመወያየት እንደሚፈታ ጽኑ አመለካከት እንዳለውም ተናግረዋል።

ወጣቱን እንፈልገዋለን ብለው በወጣቶች ዙሪያ የሚሠሩ አካላት በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባ የጠቆሙት ኬሪያ፤ የትግራይ ሕዝብ ፍትሕ እንደሚያስፈልገውና ፍትሕም መረጋገጥ እንዳለበት አሳስበዋል።

ሕዝቡ ከፍተኛ የሰላም ጥማት እንዳለበት በመግለጽ፣ ሰላምን ማረጋገጥ አለብን የሚሉ ተቋማት በሰላም ግንባታ ዙሪያ በስፋት ሊሠሩ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

በማርቆስ በላይ
++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ #ትግራይ #ሰላም #ወጣቶች #ፍትሕ #ውይይት #ኢትዮጵያ #ኬሪያ_ኢብራሂም
  • ❤ 10
  • 😁 1
More from @ethpress
  1. Oct 12, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐ19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ያስተላለፉት መልዕክት ++++++++++ ‎ ‎“ሠን…
  2. Oct 11, 2026የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ ++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ…
  3. Oct 10, 2026በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም ያለው የማጣሪያ ፋብሪካ ስራ ጀመረ +++++++++++++++ #ጋዜጣ ፕላስ-በኢትዮጵያ…
  4. Oct 8, 2026የመደመር መንግስት አዲሱ ካቢኔ #የመደመር_መንግሥት #PMOEthiopia #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
  5. Oct 8, 2026አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣…
  6. Oct 8, 2026ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን የሚኒስትሮች ሹመት አፀደቀ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የሕዝብ ተወካዮ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →