TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46388 2.4K
አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አምባሳደር ቆንጂት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በ1950ዎቹ በለጋ እድሜያቸው ተቀላቅለው ከዴስክ ኦፊሰርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት አገልግለዋል።

አምባሳደር ቆንጂት ከዮዲት እምሩ በመቀጠል በኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሴት አምባሳደርም ናቸው።

አምባሳደሯ በኦቶዋ፣ ካይሮ፣ ቴል አቪቭና ቬይና በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር፤ በአፍሪካ ህብረትና በተባባሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ መልዕክተኛ በመሆን መሠራታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ከሰኔ 2009 እስከ መስከረም 2011ዓ.ም ኢጋድ በመራው የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ላይም ልዩ አማካሪም ነበሩ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በአምባሳደር ቆንጂት ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጆች መጽናናትን ይመኛል።
  • ❤ 2
More from @ethpress
  1. Oct 12, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐ19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ያስተላለፉት መልዕክት ++++++++++ ‎ ‎“ሠን…
  2. Oct 11, 2026የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ ++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ…
  3. Oct 10, 2026በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም ያለው የማጣሪያ ፋብሪካ ስራ ጀመረ +++++++++++++++ #ጋዜጣ ፕላስ-በኢትዮጵያ…
  4. Oct 8, 2026የመደመር መንግስት አዲሱ ካቢኔ #የመደመር_መንግሥት #PMOEthiopia #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
  5. Oct 8, 2026አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣…
  6. Oct 8, 2026ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን የሚኒስትሮች ሹመት አፀደቀ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የሕዝብ ተወካዮ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →