TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46381 2.1K
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Photo
ኢትዮጵያ በተመድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንትነቷን በብቃት ተወጥታለች
++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ -ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንትነቷን በብቃት መወጣቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በ61ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ለኢዜአ በሰጡት ማብራሪያ፥ ኢትዮጵያ 47 አባል ሀገራት ያሉት የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል በመሆን ለሦስተኛ ጊዜ ተመርጣ በንቃት እየሠራች ትገኛለች።

በዚህ የአባልነት ዘመኗም፣ ከፌብሩዋሪ 23- ማርች 31/2026 በጄኔቫ ሲካሄድ በቆየው በ61ኛው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ላይ የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን የመጀመሪያውን የአመራር ኃላፊነት በብቃት ተወጥታለች።

በስብሰባው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን በሚመለከት በአባል ሀገራት የቀረቡ 38 ውሳኔዎች የተላለፉበት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም ሰባቱ ሀገር ተኮር ውሳኔዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ከሀገር ተኮር (Country Specific) ውሳኔዎች መካከል ከዩክሬን እና ሩሲያ ግጭት፣ ቤላሩስ፣ የሶሪያና ጎላን አካባቢ ባሉ ጉዳዮች፣ በፍልስጤም እና ከደቡብ ሱዳን ጋር የተገናኙ ጉዳዮች ይገኙበታል ብለዋል።

በእነዚህ ሀገር ተኮር ጉዳዮች ላይ አባል ሀገራቱ ከራሳቸው ብሔራዊ ጥቅም በመነሳት፥ የመደገፍና የመቃወም ውሳኔ ማሳለፋቸውን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያም እንደ አባል ሀገር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አቋሟን ማንጸባረቋን ጠቅሰው፥ ሀገራችን በመርህ ደረጃ ሀገር ተኮር ውሳኔን እንደማትደግፍ ገልጸዋል።

እንደዚህ ያሉ ውሳኔዎች ከዚህ ቀደም እንደነበሩና ኢትዮጵያ እንደምትቃወምም አንስተዋል።

ለአብነትም ኢትዮጵያ ችግር ላይ በነበረች ጊዜ ሀገራችን ባልተስማማችበት ጉዳይ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያዎች ኮሚሽን ተቋቁሞ እንደነበር አስታውሰው፥ ኢትዮጵያና ሌሎች ሀገራት በጋራ እንዲቀለበስ ማድረጋቸውን አስረድተዋል።

እንደዚህ ያሉ ሀገር ተኮር ጉዳዮች የሚመለከታቸው ሀገራት ሳይስማሙባቸው የሚቋቋሙ፣ የዓለም አቀፉን የወንጀል ፍርድ ቤት ሥልጣንና ሚና የሚያጣቅሱ፣ እንዲሁም የምርመራና የዓለም አቀፍ ዳኝነት ይዘት ያላቸው ናቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ እንደዚህ ያሉ የሀገርን ሉዓላዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚጥሉ ሀገር ተኮር ውሳኔዎችን በመርህ ደረጃ እንደማትደግፍ በማንሳት፥ በጉባኤው ያሳለፈችው ውሳኔም ይህንኑ እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ፍልስጤም እና የእስራኤልን በተመለከተ በተመድ መድረክ ስታራምድ የቆየችውን አቋም አሁንም ማስቀጠሏን ገልጸዋል።

የእስራኤልና ፍልስጤም የሁለት ሀገርነት መርህን እንደምትደግፍና ከሁለቱም ጋር መልካም ግንኙነት እንዳላት አንስተዋል።

ኢትዮጵያ የፍልስጤምን ሕዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንደምትደግፍ ጠቅሰው፥ ይህንንም በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባኤ የተላለፈውን የፍልስጤም የራስ ገዝነት ውሳኔ (HRC/61/L.37) ደግፋ ድምፅ መስጠቷን ተናግረዋል።

የሁለት ሀገርነት መፍትሔውም በዘላቂነት በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤዎችና በጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎች መሰረት እንዲተገበር ጥሪ ማቅረቧንም ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በጉባኤው በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ከየአር ትራንስፖርት፣ ከመርከቦች እንቅስቃሴ፣ በቀጥታ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያሳድረውን ጫናና ስጋት ለጉባኤው መግልጿን ጠቅሰዋል።

አፋጣኝ ተኩስ አቁም እንዲደረግና መፍትሔ እንዲፈለግ ጥሪ ማቅርቧንም ተናግረዋል።
  • ❤ 3
  • 👎 2
  • 👍 1
More from @ethpress
  1. Oct 12, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐ19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ያስተላለፉት መልዕክት ++++++++++ ‎ ‎“ሠን…
  2. Oct 11, 2026የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ ++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ…
  3. Oct 10, 2026በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም ያለው የማጣሪያ ፋብሪካ ስራ ጀመረ +++++++++++++++ #ጋዜጣ ፕላስ-በኢትዮጵያ…
  4. Oct 8, 2026የመደመር መንግስት አዲሱ ካቢኔ #የመደመር_መንግሥት #PMOEthiopia #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
  5. Oct 8, 2026አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣…
  6. Oct 8, 2026ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን የሚኒስትሮች ሹመት አፀደቀ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የሕዝብ ተወካዮ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →