TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46367 1.97K
"በሀገር ውስጥ መድኃኒትን የማምረት አቅም ወደ 44 በመቶ አድጓል”
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | በሀገር ውስጥ መድኃኒትን የማምረት አቅም ወደ 44 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባውን እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀውን የምርምር ማዕከል መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ እንደ መኪና እና አውሮፕላን ያሉ ቴክኖሎጂዎች ባይኖሩ ሀገር ልትቀጥል ትችላላች።

ምግብ፣ ልብስ እና መድኃኒት ግን የሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎቶች በመሆናቸው በእነዚህ ዘርፎች ራስን አለመቻል የሀገርን ሉዓላዊነት ጥያቄ ውስጥ እንደሚከት አስገንዝበዋል።

የኮሮና ወረርሽኝ በወቅቱ ያስከተለው ተግዳሮት እና መድኃኒት ከውጭ ለማግኘት የነበረው አዳጋች ሁኔታ፣ ኢትዮጵያ በእነዚህ ሦስት ቁልፍ ዘርፎች ራሷን ለመቻል ቁርጠኛ አቋም እንድትይዝ ትልቅ መነሳሳት መፍጠሩን አስታውቀዋል።

በባለፉት ጥቂት ዓመታት በመድኃኒት ምርት ዘርፍ ለውጥ መመዝገቡን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በሀገር ውስጥ የሚመረተው መድኃኒት ከ8 በመቶ ወደ 44 በመቶ ማደጉን ገልጸዋል።

በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የሚመረቁ አዳዲስ ፋብሪካዎች ደግሞ ይህንን አቅም ከ50 እስከ 55 በመቶ እንደሚያደርሱት ጠቁመዋል።

አዲሱ የምርምር ማዕከል በላቀ የላብራቶሪ ምርምር የኢትዮጵያን የመድኃኒትና የክትባት ማምረት አቅም እንደሚያሳድገው እና ሀገሪቱ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በዘርፉ ያቀደችውን ራስን የመቻል ግብ ለማሳካት ትልቅ መሠረት እንደሚሆን አመላክተዋል።

የምርምር ማዕከሉ ያለው የቴክኖሎጂ ብቃት፣ የሰው ኃይል መነሳሳት እና የተቋሙ ውበት ለሌሎች ተቋማትም አርአያ የሚሆን መሆኑን ገልጸው፣ ምርምሮች ወደ ገበያ ወጥተው የዜጎችን ሕይወት እንዲታደጉ አደራ ብለዋል።

በሄለን ወንድምነው

++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #ጤና #ራስን_መቻል #ሉዓላዊነት
  • ❤ 3
More from @ethpress
  1. Oct 12, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐ19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ያስተላለፉት መልዕክት ++++++++++ ‎ ‎“ሠን…
  2. Oct 11, 2026የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ ++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ…
  3. Oct 10, 2026በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም ያለው የማጣሪያ ፋብሪካ ስራ ጀመረ +++++++++++++++ #ጋዜጣ ፕላስ-በኢትዮጵያ…
  4. Oct 8, 2026የመደመር መንግስት አዲሱ ካቢኔ #የመደመር_መንግሥት #PMOEthiopia #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
  5. Oct 8, 2026አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣…
  6. Oct 8, 2026ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን የሚኒስትሮች ሹመት አፀደቀ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የሕዝብ ተወካዮ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →