አንዲት መነኩሴ ላይ ጉዳት ደርሷል - የአይን እማኞች
በወልዲያ ከተማ በዛሬው እለት የከባድ መሳሪያ ጥቃት ተፈፅሞ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ተናገሩ።
አንዲት መነኩሴ ላይ ጉዳት መድረሱን የገለፁት ነዋሪዎቹ፣ ጥቃቱ በማን እንደተፈጸመ አለማወቃቸውን አብራርተዋል።
የመንግስት ሀይሎች መድፍ ሲተኩሱ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ሀይሎች ደግሞ ሞርታር መተኮሳቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል።
በከተማዋ ዛሬ ጧት መንግስት ለሚያነሳው የወደብ ጥያቄ የድጋፍ ሰልፍ እንደነበር አብራርተዋል።
ነገርግን "ከግድቡ ወደ ወደ ወደቡ" በሚል መፈክር የተደረገው ሰልፍ የታጣቂዎች ተኩስ ከተሰማ በኋላ መበተኑን አስረድተዋል።
የከተማዋ አስተዳደር ሰልፉን ለማካሄድ በከተማ ሙሉበሙሉ የትራንስፖርት አገልግሎትን አስቁሞ ነበር ብለዋል።
በትናንትናው እለት የአሽከርካሪዎች ማህበራት ተጠርተው ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ምንጮቻችን ነግረውናል።
ባለፉት ቀናት በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የተለየ ይዘት ያላቸው ሰልፎች እየተካሄዱ ይገኛሉ።
በአንፃሩ በራያ የተካሄደው ሰልፍ የትግራይ ሰላም ሀይል በነዋሪዎች ላይ እየፈፀመ ነው ያሉትን ግፍ እንዲያቆምና ከተማዋን ለቆ እንዲወጣ ጠይቀዋል።
#Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #አማራ #አማራ_ፋኖ #ወልዲያ #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና
Post #7331
783


- ❤ 3