መከላከያ ወደ ኤርትራ ይገባል - አቶ ጌታቸው ረዳ
በኤርትራ መንግስት እና አጋሮቹ ላይ በጊዜ እርምጃ አለመውሰድ መዘዝ ያስከትላል አሉ።
ጌታቸው የኢትዮጵያ ጦር ወደ ኤርትራ ገብቶ እርምጃ መውሰዱ እንደማይቀር ተናግረዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም የቀይ ባህር ቀጠና ልዩ መልእክተኛ አኔት ወበር እና በኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ጋር በወቅታዊ የቀጣናው ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ገልፀዋል።
በውይይቱ ወቅት ለቀጠናው ሰላምና ዘላቂ መረጋጋት እጅግ አስፈላጊ በሆኑ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን እንዲሁም በትግራይ፣ በኤርትራ እና በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ግልጽ የሆነ የሃሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን አመልክተዋል።
አቶ ጌታቸው በአስመራ ኤርትራ ያለው አገዛዝ እና ስፖንሰሮቹ/ደጋፊዎቹ ቀጠናውን ለማወክ እያከናወኑት ያለውን አደገኛ ሚና አጉልተው ያሳዩ ሲሆን፣ ይህን እንቅስቃሴ በጊዜው ለማስቆም አስፈላጊውን እርምጃ አለመውሰድ የሚያስከትለውን አስከፊ መዘዝ እንዳስረዱ ገልጸዋል።
ውጥረቱ የበለጠ እንዳይባባስ ለመከላከል፤ የመረጃ ልውውጥ አጠናክሮ ለመቀጠል እንዲሁም በቅንጅት ለመስራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
#Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን #አቡነ_ሳዊሮስ #ተመስገን_በየነ #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና
Post #7309
1.1K

- 👍 3
- ❤ 2
- 😱 2
- 🔥 1