መከላከያ የህወሓት አመራሮችን መማረኩ ተገለፀ።
የኤርትራ ወታደሮች ከተማረኩት ውስጥ ይገኙበታል ተብሏል።
ስማቸው ያልተገለፀ አምስት የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል።
አመራሮቹ በመከላከያ ቁጥጥር ስር መዋላቸው የተሰማው አራቱ መቀሌ ውስጥ፣ አንዱ ከመቀሌ ውጭ መያዛቸው ተጠቁሟል።
ከመቀሌ የተያዙት የድርጀቱ አመራሮች ኬላ ላይ ለመውጣት ሲሞክሩ እንደሆነ ነው የተገለጸው።
እነዚህ የህወሀት አመራሮች አሁን ላይ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ሆነው ለፌደራል መንግሥቱ ጥሪ ማቅረባቸው ተሰምቷል።
በአንፃሩ የኤርትራ ወታደሮች በአዲግራት በኩል በነበረው ውጊያ ከህወሓት ታጣቂዎች ጋር ተይዘዋል ተብሏል።
የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ስር ውለዋል ስተለባሉት ወታደሮቹ የሰጠው ማብራሪያ የለም።
#Ethiopia #ethiopia_today #ethiopian_news #addis_ababa #amharic_news #borkena_news #ኢትዮጵያ #ትግራይ #ጦርነት #ህወሃት #ምርኮ #መቀሌ #አብይ_አህመድ #አማርኛ_ዜና #ዜና #ቦርከና_ዜና
Post #7240
1.04K


- ❤ 3