የአለሙ ገዢ ሆኖ ሳለ ለሰው ልጅ መዳን ሲል ከታላቅ መንበር ፍቅርን ሰውን መውደድን ሞቶ ለማሳየት ወደምድር መውረድ አለምን በደም ለመዋጀት መመምጣት ወደቀድሞ ቦታው ይመልሰው ዘንድ በፈጠራት ማህፀን ማደር ከአይምሮአችን በላይ ነው::
ያንተን ስራ ያንተን የፍቅር ጥግ መክፈል የማንችለው የእዳችን ማስተሰሪያ ነው::
አምላክን ለመሸከም የተገባ መሆን ሁሉንም ነገሮች አሟልቶ መገኝት ምንኛ ድንቅ ነው::
ሰማይና ምድር በፊቱ እንኳን ንፁህ አይደሉም ለሚባልለት ጌታ ማደሪያ የበቁ ሆኖ መገኝት እንዴት ያስገርማል::
አምላክን ፈጣሪን ልጄ ብሎ መጥራት እንዴት ከአይምሮ በላይ ነው::
መላዕኩም እንዴት ሆኖ ይሆን ሲያነጋግርሽ ምን ያህል ተጨንቆ ይሆን::
በትህትና ቃል ይኩነኒ በከመ ትቤ ለኒ ብለሽ አምላክን ለመሸክም የመላኩን ቃል ተቀብለሽ አምላክን ወልደሽ የሰጠሽን የመድሃናችን ምክንያት ሆንሽን::
ህይወት አኗኗርሽ ትምህርት ቤታችን ነው::
እንወድሽ እናከብርሽ እናመሰግንሽ ከፍ ከፍ እናደርግሽ ዘንድ ምክንያታችን ብዙ ነው::
እኛም የመዳኛችንን ቃል ደጋግመን እንሰማለን #ይኩነኒ_በከመ_ትቤ_ለኒ አለሙ ሁሉ የዳነበት ቃል::
በልጅሽ ቸርነት በአንቺ ምልጃ ዘመናችን በቤቱ ይፈፀም ዘንድ እንለምናለን::
እንኳን ለልደት በዓል አደረሳችሁ::
@jahABP ነኝ