TGViewer
Channel Public Channel
Phenomenal pictures & graphic design

Phenomenal pictures & graphic design

@abpgd

FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Subscribers
1.08K
Photos
1.8K
Videos
8
Links
16

Showing posts older than #1935 · Back to latest

Older Posts 20 shown
Post #1934 699
ይቺን ተጋበዙልኘ 👣👣👣👣👣👣
Post #1931 802
እንኳን አደረሰህ ብሎ ቤቱ አክብሮ ጠርቶህ በወንድ እጁ ራሱን አብስሎ
የሚገርም የሚጣፍጥ😋😋😋 እራት የሚያበላ ጓደኛ ካለህ አንተ በእውነት እድለኛ ነህ፡፡

ማቲሻ የወደፊቷ ሚስትህ ነች የታደለችው በጠዋት ስትነሳ ቆንጅዬ ቁርስ ሰርቶ የሚጠብቅ ባል ነው ያላት፡፡

👏👏👏👏በርታልኘ እግዚአብሔር ያክብርልኘ ወንድሜ፡፡
Post #1930 842
AB PHOTOGRAPHY

ሁሌም መስከረም አንድ ቀን ሲል መሔድ እመኘ ነበር በብዙ ምክንያት አይሳካልኘም፡፡

ዘንደሮ አልተሳካልኘም መሰላችሁ🙏🙏🙏🙏

ሊቀመላኩ ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን

@ABPGD @ABOGD @ABPGD @ABOGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #1929 873
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼❤️❤️🌼❤️🌼🌼

AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

እንኳን አደረሳችሁ

ከባለፈው አመት እና በዛሬ አመት ላንተ ምን የተለየ ነገር አለው ብትሉኘ የመጀመሪያ መልሴ በእግዚአብሔር አምላክ ላይ ያለኘ እምነት መጨመሩ ነው የምላችሁ፡፡

በእሱ ላይ ያለኘ እምነት ከትላንት ዛሬ የበለጠና የጠነከረ ነው፡፡

ዋናው በዓል መኖር ነው ይቺን ቀን ያላዩ አያሌ ሰዎች አሉ እና እያን መርጦ ለዚች አዲስና አይተናት ለማናውቃት ቀን ስላደረሰን ልናመሰግነው ይገባል፡፡

ሁሌም ከእንቅልፌ ስነሳ አይኔን ስገልጥ አጠገቤ ያሉትን ነገሮች ማየት ስችል ዛሬም በህይወት አለሁ የድንግል ልጅ ዛሬም ኑር ብለህ ፈቀድክልኘ ኧረ ተመስገንልኘ እልላለሁ ብታምኑም ባተምኑም ሁሌ የቀኑ መጀመሪ ቃሌ ይሔ ነው፡፡

አለን አለህ አለሽ አላቹ??

ስለዚህ ማመስገን የመጀመሪያ ስራችን ይሁን፡፡ ከዛ ሁሉም ትርፍ ነው፡፡

ትላንት አንድ ሰው የአለምን ሀብት ሰጥቶ ዛሬን ግን ማየት አትቹልም ቢለን እንስማማ ነበር?? አንስማማም ውዷ ስሚኘ እስኪ ይህ ማለት እኮ የአንቺ ግምት ከአለም ሀብት የበለጠ ነው ማለት ነው አንቺ እኮ ውድ ነሽ ደስ አይልም፡፡

ተስፋ መቁረጥ አይደለም ዛሬን መኖር ነው ለነገ የሚያደርሰን አንተ የሌለህበት ስንት የማያምር ነገር አለ መሰለህ.....ታስፈልገናለህ......

ፍቅር ስማኘማ ኑር "ባታምንም ለከንቱ አልተፈጠርክን የዛሬ ህይወትህ ባይሞቅም ነገም ካንተ ውጪ አይደምቅም ታስፈልገናለህ፡፡"

እቅድሸሸ እንዲሳካ እመኘልሻለሁ አንድ እርምጃ ወደፊት እንድትጓዢ እፈልጋለሁ...የሚጎትትሽን ሱስ ትተሽ ራስ ወዳድነትሽን ጥለሽ መልካምነትን ተላብሰሽ ድርቅ ደሚያደርግሽን አቁመሽ መጥፎ መገለጫሽን በሙሉ ትተሽ "ነቅቻለሁ ተርፌያለሁ ራሴን ላድን ቆርጫለሁ ልኩላይ ብርሃኑ ላይ አይኔ ላይፈዝ ጨለማው ላይ ልፈልገው ከዋለበት ፍፁም ፍቅር ከሞላበት" እንድትይ እፈልጋለሁ ይህ አዲስ አመት ያንቺ ነው ውድ ስሚኘ ተጠቀሚበት፡፡

አምላካችንን የምናስደስትበት የሱ ምርጥ እቃ እንድንሆን ዘመናችን በቤቱ ይፈፀም ዘንድ እንለምነው በቸርነቱ አመታትን ያቀዳጃልና ክብር ምስጋናም ይገባዋል፡፡

ይኩነኔ ብላ ይህን አለም ካለመኖር ወደመኖ ያመጣችልን መሰላላችን ወደ እሱ መቅረቢያችን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብር ምስጋና ይገባታል መሐረኒ ድንግል እባክሽ ሁሌም ከኛ ጎን ሁኚ አትለይን፡፡

ቅዱሳን መላዕክት ፃድቃን ሰማዕታት ዘወትር ለኛ ይማልዳሉ እንዳንጠፋ ዘወትር በፊቱ ለኛ ሲሉ በመንቀጥቀጥ ይቆማሉ ፀሎታችሁ አሁንም ይጠብቀን፡፡

በመልካምነት አምናለሁ ላለው ብቻ አይደለም ስንሰጥም ነውና የሚጨመርልን ባለን ነገር ሰውን ከማስደሰት ለአፍታ መስነፍ የለብንም ምንም ተፈጠረ ማንም ሔደ ማንም መጣ እኛነታችንን መልቀቅ የለብንም ሴቶች አህቶቼ እባካችሁ በሌላ ሳይሆን በአይምሮአችሁ ማሰብ ጀምሩ ልባችሁን አዳምጡ #ክብርሽን ጠብቀሽ ያዢ እባክሽ፡፡

ፍቅር ከክፋት እጅጉን የራቀ ነውና የፍቅር ሰው እንሁን፡፡

በድጋሚ መልካም በዓል፡፡

@jahABP ነኘ 😍😍😘😘😘🙏🙏🙏

የድንግል ልጅ ማረን ይቅርም በለን በየዘመኑ፡፡

መልካም ቀን ፡፡

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
Post #1928 772
Audio
ዘበናይ

ዳን አድማሱ

ከዚ በፊት ሰምተሽው ከሆነም እስከዛሬው በተለየ መልኩ ስሚው

"አያረጅም ዘመን አልፎበቶ ቅን ውበቷ
በእውነት #ክብር የተረጋጋው ሴትነቷ"

@jahABP ነኘ😍😍🙏🙏😊😊
Post #1927 741
1..........................2....................3
Post #1926 813
ሴቶች ግን ይኼን ዘፈን ሰምተውት ይሆን እላለሁ.....የምሬን ነው ከልቤ ነው እንደው እራሳቸውን ለትንሽ ደቂቃ ያዩበታል ብዬ አስባለሁ። አሁን ላይ የሆነ ልክ ያልሆነ ነገር አለ ለራሳችውም ይታወቃቸዋል ብዬ አሰባለሁ።

እና ይሔን ሙዚቃ ሰምተው ትንሽም ብትሆን ይስተካከሉበታል የሚል ሙሉ እምነት አለኝ።

ተጋበዙልኝ የወደፊቷ ሰምተሻል አስቢበት @jahABP ነኝ

ጠብቁኘማ👣👣👣👣👣
Post #1925 883
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም በጤና አደረሰዎት፡፡


#LUXURY ኮስሞቲክስ ለናንተ ለውድ ደንበኞቹ ከካናዳ ከአሜሪካ ያስመጣቸውን #ኦርጅናል ኮስሞቲክስችን እንካችሁ ይላል
🌹🌹🌹🌹🌺🌼🌼🌼🌻🌻🌻🌷🌷


ይምጡና ይጎብኙ ⭐️⭐️⭐️⭐️

አድራሻችን፡- #ቦሌ_ብራስ_ከስኮፕ_አይስክሬም_አጠገብ፡፡
ስልክ ቁጥር:- +251 922 46 92 17

በቴሌግራም ቻናል ወዳጆች እንሁን👉👉👉👇👇👇👇👇

https://t.me/luxcosmo
መልካም አዲስ አመት ይሁንላችሁ
💚💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️❤️
Post #1922 818
Track 12Unknown artist
በሩ ተዘግቶ ሳይጨልም
በረግረጉ እግርህ ሳይሰጥም
ጥቂት ቀረህ ገና መንገድህን አቅና
ገልጠህ አይንህን እግርህን አንሳና

#በል_አሁና_አምነህ_ፅና
#ቆይ_እንዳትል_መስሎህ_ቀንህ_ገና
*በቃ አትበል ግን ምሽት መጣ
ጥልቁ አይሞቅም ተነስ ፍጠን ውጣ

ለምን ታስፈርድ በራስህ
ማወቅ ሳትፈልግ ለነፍስህ
#ሕግ_አድምጠህ_ምን_ባታውቅም
#መች_ተባልክ_አትጠየቅም

#ሳያውቅ_ላጠፋ_አውቆ_ለከፋ
#ህጉ_እንደው_ያው_ነው_አይጠብ_አይሰፋ

#አትምረጥ_አለማወቅን
#አውቀህ_አጨፍን_እይ_ወደቅን
ተስፋ የለም ከዚ ሌላ
በቅን መሳይ እንዳትሞት ኀላ

ሰው በጁ ሰራ እንጂ የሚፈረጅ
ማወቅ ፋንታው ሳለ ቢንቅ ተጎጂ

ሳያውቅ ላጠፋ አውቆ ለከፋ
ሕጉ እንደው ያው ነው አይጠብ አይሰፋ

አልበም #እሳቱ_ሰዓት
🎤#ልዑል_ሀይሉ


#ግጥም_ዜማ_ቅንብር
#ታላቁ_ኤልያስ_መልካ

@jahABP ነኘ🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂👣👣👣

አስተያየታችሁን አድርሱኘ
Post #1920 713
1........2.......3
Post #1919 829
ይህን ዘፈን ስሰማው እፈራለሁ


እራሴን የቱ ጋር ነው ያለሁት ብዬ እፈልጋለሁ

መጥፎ ነገር ከማድረግ እጥፉኑ እርቃለሁ እፀየፈዋለሁ እሸሸዋለሁ ነገስ ብዬ አስባለሁ
ብሞትስ የት ሆኜ ምን አይነት ሰው ሆኜ

እዚህ ሙዚቃ ውስጥ ትክክለኛው ማንነቴ ምን መሆን እንዳለበት እስለዋለሁ አስበዋለሁ....

#ግጥም_ዜማ_ቅንብር
#ታላቁ ........ #ኤልያስ_መልካ

ጠብቁኘማ👣👣👣👣👣👣


ወዳጄ ፈጣሪን በጣም ነው የምፈራው፡፡
Post #1917 890
#ያ_ባለቅኔ

መቼ ይሆን ቀኑ

መነሻ ዘመኑ

ያ ባለቅኔ ያ ግጥም ገጣሚ
ልዩ አይነት ዜማ አስደሳች ለሰሚ
ቅኘት ስልት አውጥቶ
የሚያሰማን ከቶ

የአሁኑ ግጥማችን አንድ አይነት ሆነና
ችክ ምርር አለን ቅያሪ ጠፋና
ወዝ ለዛ አጣ
ሆነብን ቆምጣጣ

ያ ባለቅኔ ቶሎ በተነሳ
ግጥማችን ታድሶ እንደሌላው ጎሳ
ቅኔ ተፈልስፎ
በታየ ተዘርፎ፡፡

#አሰፋ_ገብረማሪያም_ተሰማ
(የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ደራሲ)
Post #1913 1.02K
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ሳቀች ከልቧ ሳቀች

የምር ደስ ትላለች 😍😍😍😘😘

እኔ:- ይቅርታ አልኳት

እሷ፡- ለምኑ

እኔ፡- አይ እኔን ስላልመሰለኘ ነው ዝም ያልኩሽ.....

እሷ:- ታዲያ እሱ ይቅርታ ያስጠይቃል እንዴ??

እኔ፡- 😳😳ይቅርታ አያስጠይቅም እንዴ 🤔🤔እሺ ይቅርታ በማያስጠይቀው ይቅርታ ስላልኩሽ #ይቅርታ

እሷ፡- ሀይለኛ ሳቅ😂😂😂😂😂

ታክሲውን በጠበጠችው

አፈርኩኘ 🙈🙈🙈🙈

#ከቦሌ_ጫፍ_እስከ_አራት_ኪሎ

የቴሌግራም ልቦለድ በቅርብ ቀን

@jahABP ነኘ
Post #1912 45.7K
ክፍል 2

ኡኡኡኡኡኡኡኡኡ....ከወደውጪ ድምፅ ተሰማ፡፡ አስር አለቃ ጎረቤታቸውን በዱላ አናቱን ብለው በሩ ላይ ደፍተውት ነበር፡፡

ሰይጣን አጀንዳውን ይዞ አስር አለቃ ግቢ ሲደርስ ነገር ተደበላልቆ ጠበቀው፡፡ ጉዳዩን በጥንቃቄ አጣራና አጀንዳው ላይ እንዲህ ሲል ከተበ "የአስር አለቃው ጉዳይ ከእቅድ በላይ ተፈፅሟል፡፡"

ሦስት ፖሊሶች ኮሌታቸው ጨምድደው ወደያዟቸው አስር አለቃ ጆሮ ጠጋ አለና "አንተ ሸፋፋ! ስማ..! አሁን በግድያ ሙከራ ዘብጥያ ትወርዳለህ የተበደረው ጎረቤትህ ተሽሎት ወደ ቤቱ ይመለሳል..፡፡ ያች አንቋራሪ ልጅህም የትም ስታንቋር

ር ስለምትውል ቤትህ ሰው የለም፡፡ ሚስትህና ጎረቤትህ ብቻቸውን እዚህ ሰፊ ግቢ ራስህ አልጋ ላይ...ሂሂሂሂሂሂ ቂቂቂቂቂቂ አይ ሸፋፋው!!

ይልቅ ሚስትህን ዓይንህ እያየ ከምትወሰድ አንዱን ፖሊስ በካራቴ ድፋውና አምልጥ...ወታደር አይደለህ...? አስር አለቃ አይደለህ?.... ኮማንዶ ነኘ እያልክ በየጠላ ቤቱ ስታወራ አልነበር...? ወይስ ዝም ብለህ ስትወሽክ ነው...፡፡"

አስር አለቃ ቀስ ብለው ከጎናቸው የቆመውን ፖሊስ ተመለከቱት፡፡ክስት ያለ ነው...በዛ ላይ የያዘው መሳሪያ የከበደው ይመስላል፡፡ ሁለቱም ፖሊሶች ቢሆኑ ያን ያህል የሚስፈሩ አይደሉም ቀድረ ቀላል ነገር ናቸው፡፡ " ይሔኔንንስ መሣሪያውንም መንጠቅ አያቅተኘ " ሲሉ አሰቡ፡፡ ፖሊሶቹ አስር አለቃን እያጣደፉ ወደ ጣቢያ ወሰዷቸው፡፡

ዷ....! ዷ............መንደርተኛው ከሩቅ የተኩስ ድምፅ ሰማ

"ምንድነው....?"

"እስረኛ ሊያመልጥ ሞክሮ.....ፖሊሶቹ እግሩን ሰንክለው አቆሙት.....!

ሰይጣን በሳቅ ፍርስ አለ፡፡ እናም አጀንዳው ላይ እንዲህ ሲል ፃፈ "የእግሩ ጉዳይ አልቋል አሁን ነፍሱን ማንሻፈፍ ይቀረኛል!!"

ከዛም ሰይጣን ቀይ እስኪሪቢቶ አወጣና እየተፍነከነከ እንዲህ ሲል ፃፈ

"አስር አለቃ አምሳ አለቃ መቶ አለቃ ሻለቃ ጄነራል ሚኒስተር ...ጠቅላይ ሚኒስተር ሁሉም እግር አላቸው፡፡ እንኳን እነርሱ አገርም እግር አላት ስንፈልግ እናንሻፍፋታለን!!!"

ደራሲ #አሌክስ_አብርሃም
#ዙቤይዳ ከሚለው መፅሐፍ

#እግር_በእግር
ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ
😍😍😍🙏🙏🙏
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #1911 833
ክፍል ሁለት 👣👣
Older posts →
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →