#ያ_ባለቅኔ
መቼ ይሆን ቀኑ
መነሻ ዘመኑ
ያ ባለቅኔ ያ ግጥም ገጣሚ
ልዩ አይነት ዜማ አስደሳች ለሰሚ
ቅኘት ስልት አውጥቶ
የሚያሰማን ከቶ
የአሁኑ ግጥማችን አንድ አይነት ሆነና
ችክ ምርር አለን ቅያሪ ጠፋና
ወዝ ለዛ አጣ
ሆነብን ቆምጣጣ
ያ ባለቅኔ ቶሎ በተነሳ
ግጥማችን ታድሶ እንደሌላው ጎሳ
ቅኔ ተፈልስፎ
በታየ ተዘርፎ፡፡
#አሰፋ_ገብረማሪያም_ተሰማ
(የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ደራሲ)
Post #1917
890
