TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #2433 416
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN
#መዓዛ_ምግባር

የክፎች መዓዛ ምግባር እንዳይሸትህ አፍንጫህን ያዝ::

እንዲሁም ክፉ ተናግረው እንዳያናግሩህ አፍህን መዝጋትና ለግፍ ሳቃቸው ተካፋይ እንዳያደጉህ ከንፈርህን መግጠም እግዚአብሔር ላዘጋጀልህ ለዘለዓለም ደስታ ብቁ ሊያደርግልህ ይችላል:: ይህንንም የመሰለ ምግባራዊ ጥንቃቄ በእውነት ደረጃ ላይ ሊያውልህ መቻሉ እርግጥ ነው::

መድኃኒት ያቀማመጥና ያያያዝ ጥንቃቄ ሲጎድልበት መርዝ ይሆናል:: ሰብአዊ ኑሮም ይህን የመሰለው ሕይወታዊ ድርጅት ሳይደረግለት ቢቀር የመጥፎ ዕድል ባልደረባ አድርጎ ያስቀራል::

ሰው በምግባሩ በኩል ቅዱስ ለመሆን ከፈለግ ሰይጣን በበኩሉ ያስወጣቸውን ደንቦች ለመቃወም ሲችል እሱ ከክፋት የራቀውን ያህል ክፋት ከሱ እየራቀ መሔዱ የታወቀ ነው::

የዓለም ክፋት ትዝ እያላቸው ከዓለም የሚሸሹትን ደጋግ ሰዎች እንኳ ሳይቀር ሐተታውን ለመከታተል የማይቻል ፈተና ቢደርስባቸውም በመጨረሻው ድልን ለማግኘት መቻላቸው የታወቀ መሆኑ አይዘነጋም::

ለምሳሌ:- #አባ_መቃርስ የሚባል መንፈሳዊ አርበኛ ሰይጣን ይሠራው ዘንድ ደግ አስመስሎ የሚያመጣውን የክፋት ሥራ ሁሉ እየተቃወመና ዘወትር ዝንባሌው ወደ ደግነት እየሆነ ቢያስቸግረው መቃሪ መቃሪ ብሎ ጠርቶ ዛሬስ በእውነቱ አሸነፍከኝ አለው ይባላል::

የደግነት አርበኞች ሁሉ የመጨረሻ ድላቸው እንደዚህ ነው::

መንፈሳዊ ጦርነት ዘወትር ድልን ማግኘት አለበት:: እንደ ሥጋዊ ጦርነት ድል ብሆንም ከዱር ገብቼ በሽፍንነት እከላከላለሁ ሊባል አይችልም:: ብማረክም በወጆ እለቀቀቃለሁ ተብሎ ተስፋ የሚጥሉበት አይደለም::

በሥነ ምግባር ጠንክሮ ተከላክሎ ጠላትን ከማሸነፍ በቀር በሰይጣን ጥፍር ከተያዙ በኃላ ሌላ ማምለጫ የለም::

እንደ ቆሮንቶስ ፍፁም ብሕትውና የተደረገበት ገዳም የለም:: እንዲሁም ሰይጣን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት የሆነውን ድል በማንም ፊት ሆኖ አያውቅም::

ከሰይጣን ጋር በትሩፋት የሚዋጋ ቶሎ ልብቃ ቶሎ ክንፍ ላውጣ ማለት ገና የወጣኒነትን ደረጃ ሳያልፈው ሰይጣን በምትሃቱ ጠልፎ እንዲወድቅ ያደርገዋል:: ማንኛውም ስራ ይህን በመሰለ ዕንቅፋት መሰናክል ስለምይቀርለት ሁሉን ነገር አስተውሎ ማድረግ ይጠቅማል::

ኃጢያት የዲያቢሎስ አመጽመ ርስት ነው በል በል የሚልህን አሳብ ተዋግተህ ድል ያደረግህ እንደሆነ የጽድቅህ መገለጫ በዚያ ጊዜ ነው::

አሰሪ መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ ሰይጣን አይደለም:: ስለዚህ ከእንደዚህ ያለው አሠሪ ለመለየት አሰናባች የሆነ ክፉ ምግባር አይኑርህ:: ምዝለቂያህና መውጫህን ተመልከት:: መግቢያህንም አስተውል:: ፍፃሜህን አትዘንጋ:: ልብ አለና ልብ የሌለህ አትሁን:: ሰው ነህና ከሰውነት የወጣ ስራ አትስራ:: ነገርህ ሁሉ ጨው ያነሰው ፍትፍት አይሁን:: ምግባርህን ያረረ ዳቦ አታድርገው:: ከከንፈርህም የሬት ልጋግ አይዝነም ::

ወጣት ሆይ ነሆ ለጥበብ ተጠርተኃል:: ጥበብም ዕድመኛ አድርጋሃለች:: አስከትላህ ወዴት እንድምትሔድ መንገዱ የሕይወት ነው:: መድረሻው የክብር ሥፍራ ነው:: ፈሪሃ እግዚአብሔር ለልብህ እንደከንፈር መዓር ይሁነው:: ሰው እንዳይሆን የለምና ንገ የምትሆነውን ዛሬ ለነገ ኑሮ ዋዜማ ነው:: ይህ ሁሉ ሲሆን የምትከተለውም የሚከተልህ የአምላክ ሕግ ነው::

ለሁሉም ነገር ዋና ስራ አስኪያጅ ግብረገብነት ነው:: ግብረ ገብ የሆነ ሰው ትእዛዛት ሁሉ አይከብዱትም:: ግብረ ገብያልሆነ ግን እንኳን ከባዱ ትእዛዛትና አነስተኛውም ቢሆን ስለሚከብደው ሲያዝዙ ይቆልፈዋል:: በግድም ሆነ በውድ የታዘዘውን መፈፀሙ ላይቀር ይፍተለተላል ይተሻሻል::

ስለዚህ በብሩህ ገጽ ትዕዛዝን ተቀብሎ መሥራት ያስመሰግናል:: ያስሾማል ያስሸልማል ይህ እድል ህይወተ ነፍስንም ይከተላል: የዚህም ሁሉ የቅርብና የሩቅ መነጥሩ ሃይማኖትና ምግባር ነው:: በጎ ምግባር ካለህ በፊትህ ዕንቅፋት አያጋጥምህም:: በኃላ አስጊ የለብህም በደስታ የተከበብክ በይባቤ የታጀብክ ሁነህ እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር ለወዳጆቹ ወዳዘጋጀው ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ትችላለህ::

ጥንት ጠላታችን ዲያቢሎስ እጅ ባይሰጥም ለሚያቀርብልን ክፉ ስራ አለመሸነፍ የማሸነፍ ያህል ነው::


#ሥነ-ምግባር

ተፃፈ #ከወልድ_ጊዮርጊስ_ወልደ_ዮሐንስ

አብይ የማርያም ልጅ ነኝ

ለንባብ እንዲመች አድርጌ አቀረብኩት

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →