AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
#ጠንካራ_እምነት_ሊመጣ_የሚችለው_የእምነት_ጀግኖች_አባቶቻችንን_የሠሩትን_አብነት_በማድረግ_ነው::
በአባቶች ዘመን ለእያንዳንዷ የሃይማኖት ነጥብ ብሔራዊም ሆነ ዓለም አቀፋዊ ጉባዔያት ይጠሩ ነበር:: በዚህ ጉዳይ ላይ ቅዱሳን ሃይማኖታቸውን እንዲጠበቅ ትክክለኛውን መሠረታዊ ትምህርት እንዲታወቅ ድንቅ የሆነ ሚና ተጫውተዋል::
የሚያገኙት ግላዊ ጥቅም ሣይኖር በግል የሚጎዱበትም ነገር ሳይኖር ምንቸገርኝ ያሉበት አንድም ጊዜ የለም::
ክርስትና ፍቅር ነውና ቅዱሳንም በፍቅር ውስጥ ሥላሉ ሁሉ ነገር ያሳስባቸዋል:: የሌላው ጭንቀት ጭንቀታቸው ችግሩም ችግራቸው ሆኖ ለአንዲት ቤተክርስቲያን ሲሉ ሕይወታቸውን ለመስዋትነት አቅርበው ያለዕረፍትና ያለመሰልቸት ሠርተዋል::
ቅዱሳን ምን ያህል እንደተጋደሉ ግድ ሊሰጠን ይገባል:: ቤተክርስቲያን በእውነትኛ ሃይማኖት ጥላ ስር የተሰበሰቡና ትክክለኛ ትምህርቷን የሚከተሉ ሰዎች ማህበር እንጂ የወገን ወይንም የወገናዊነት መሰባሰቢያ አይደለችም::
በየዘመናቱ ቅዱሳን ሠማዕታት የተሰቃዩበትን የተገረፉበት የተሰየፉበት ምክንያት ሃይማኖት እንጂ ሌላ እንዳልነበር አስተውል::
ይህን ደግሞ #በየገድሎቻቸው ተፅፎ ምስክር ሆኖ እናገኘዋለን::
ለምሳሌ:- ቅዱስ አትናቲዎስን ብንመለከት አራት ጊዜ ከፓትርያርክነት መንበሩ ተሠዷል በጣም አስፈሪ የነበሩ ክሶችን ሲከሰስ ሲፈረድበት ብሎም "አትናቲዎስ አንተን ዓለም ሁሉ ጠልቶሃል " ሲሉት " #እኔም_ዓለምን_ጠልቼዋለሁ " ብሎነበር የመለሰላቸው::
ዛሬ ግን በጋብቻ ወይም በፍቺ ሃይማኖት በቀላሉ ይቀየራል:: በግድ የለሽነት ወይም ባለማወቅ ከቤተክርስቲያን አገልጋዮችና አባላት ባለመስማማት ብቻ ቤተክርስቲያንን ትምህርቷን ጥሎ የሚወጣው እጅግ ብዙ ነው::
ቅዱሳን ለሃይማኖታቸው ምን ያህል እንደተጋደሉ ለእርሱ ግድ አይሰጠውም:: ምክንያቱም ይህ ሁሉ መስዋትነት የተከፈለበት ሃይማኖቱን የሚመለከተው በግድ የለሽነት ነው ያለፈው ተጋድሎ ረስቶ ስለ እምነት ወይም ስለሃይማኖት ልዩነቶች ምንም ማሰብና መጨነቅ አይፈልግም::
#ቅዱሳንን_የናቀ_ያ_ትውልድም_ሆነ_የዛሬው_የተነቀፈ_ነው::
ቅዱሳን በደግነት በጥሩ ምግባር የደረሱበት ከፍተኛ የመንፈሳዊ እድገት ደረጃ አንተን ዛሬ ባለህበት እንዳትታበይ ለሚበልጠው እንድትጥርና እድገትህ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው:: በፊትህ ያለው መንገድ እረጅም ነው:: ነገር ግን የሚሰጥህ ጸጋ በእጅህ ልትቀበለው የቀረበ በመሆኑ ቅዱሳንን እግር በእግር እየተከተልክ በመከራ በፈተና ውስጥ እንኳን ቢሆን በቁርጠኝነት ማለፍ እንድትችል ያበረታሃል::
ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! በነፍስህ ጽናትና እምነት ለመትከል እና የማይናወጥ የማይከፋፈል ክርስቲያን ለመሆን የቅዱሳንን ሕይወት የሚናገሩትን ቅዱሳት መጻህፍት ማንበብ ያስፈልግሃል::
#ገዞ_ወደ_እግዚአብሔር
#በብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
ትርጉም #ዲያቆን_ግርማ_ባቱ
ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ
#አብይ_የማርያም_ልጅ ነኝ
መልካም ምሽት
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #2429
393