እውነታው ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ ያደርጉሃል:: ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሃል::
ከሰማሃቸው ደግሞ እራስህን የመሆን እድል አይሰጡህም:: ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረቢያ ይስላሉ:: ልብህን ከከፈትክላቸው የድርሻቸውን ጠርበው ቅርፅ አልባ ያደርጉሃል::
.
.
.
መስጠት ከመትረፍ አንጀት የሚፈልቅ ወይም ከመብዛት ማዕድ የሚዘገን አልያም ከመበልፀግ ማህፀን የሚወለድ እንዳልሆነ አውቃለሁ::
መስጠት ከመንፈስ እንጂ ከሌጣ እውቀት የተጋባ መክሊት አይመስለኝም::(መክሊት ያልኩት መስጠት ከምግባር ስለሚልቅብኝ ነው::)
.
.
.
ዛር እንዳለበት ባለውቃቢ አብሮኝ እንዳላበደ የሚያደርገኝ ጠፍቶት በስሜት እንዳልሰከረ የሱ እብደት ጎበዝ ሲያስብለው የኔ ያለመሽኮርመም ብዙ ወንድ የምታውቅ ያስብለኛል::
.
.
.
ግልፅነቴ ደንቆት አንቺን ያገኝ ወንድ አፈሰ ባለኝ ቅፅበት ለምን ታዲያ ለምን አንተ አታፍስኝም? ስለው ሴት ልጅ እንዲህ አትልም ይለኛል::
.
.
.
ሀይማኖቴ ፍቅር ነው:: የሰው ልጅ ሁሉ መውደድ:: ራሴን እወዳለሁ:: ለዛ ነው ሌሎችን የሚወድ ልብ ያለኝ:: ለራሱ ፍቅር የሌለው ለሌላው ተርፎ የሚለግሰው መውደድ አለው ብትሉኝ ያንቀኛል:: በሰውኛ ልኬት ሰውን የመውደድ ጣሪያ ራስን ከመውደድ ልክ መሆኑን ለማሳየት ይመስለኛል ክርስቶስ ከህግ ሁሉ የበላይ ህግ የትኛው መሆኑን ሲጠየቅ " ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ" ያለው::
የፈጣሪ ትርጉሙ ለኔ ፍቅር ነው:: የማላየውን ፈጣሪ ማምለክ እና መውደድ በአምሳሉ በፈጠራቸው በሰዎች ሁሉ ውስጥ አለ ብሎ ማመን እነሱን ማክበርና መውደድ ነው::
#ፍቅር_ከክፋት_በብዙ_የራቀ_ነውና_ለክፋት_የሆነ_ልብ_የለኝም::
.
.
.
የሚያውቁኝ የሚመስላቸው ሰዎች ብዙ ሲሉ እሰማለሁ:: ዳሩ እንኳን ሌሎች እራሴም ስለራሴ ነኝ ያልኩትን ላልሆን እችላለሁ::
.
.
.
ሰዎች በየቦታው ፍፁም ትክክል መስሎ ሲታዩ ሰውኛ አይመስለኝም:: ከራሱ እየተቧቀሰ አካባቢው በቀረፀለት የትክክለኛነት ሳጥን ውስጥ የሚንፈራገጥ ሰው ራሱን ያጣ አሳዛኝ ይመስለኛል:: ለእያንዳንዱ ነገር የሚጠነቀቅ ሰው እራሱን እንዳልሆነ ነው የሚገባኝ:: ራስን መሆን እርማት አይጠይቅም:: ጥንቃቄም አያሻም:: መጠኑ ቢለያይም ሁላችንም ጋር ጥቂት እብደት ጥቂትም ስህተት ጥቂትም ፀፀት እና ጥቂትም ውድቀት አለ ብዬ አስባለሁ::
.
.
.
በልጅነቷ አባቷ ሲሞቱ እናቷ ለቅርብ ወዳጃቸው ለአዳዳ እንዲያሳድጟት በአደራ ሰጥተዋት ነው ዛሬ ከእናቷ በላይ የምትወዳቸው አዳዳን ያገኘቻቸው:: ምንም አይነት የደም ትስስር እንደሌላቸው ማውራት አትፈልግም የሴትየዋን ጥሩነት በዝምድና ትስስር ስትለውሰው ግራ ያጋባኛል:: በምን ሒሳብ በደም መቀላቀሉ የሴትየዋን ውለታ እንደሚያከብደው አይገለጥልኝም:: እንደ እኔ እንደውም ያለ ምንም የደም ግምድ ድግ መሆናቸው ዋጋቸውን የሚጨምረው ይመስለኛል::
#ጠበኛ_እውነቶች_በሜሪ_ፈለቀ
ምን አይነት ደስ የሚል አፃፃፍ ነው ቀጣይ ስራሽን በጉጉት እንጠብቃለን::
አብይ የማርያም ልጅ ነኝ @jahABP
ይህን መፅሐፍ ከመደርደሪያዬ ላይ ሳነሳ እነዚህን ሳላነብ እልቀርም .........እንቀጥላለን
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #2422
433