TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #2334 793
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

አብዬ አለችኝ........ድክም ባለውና መጠጥ ባኮላተፈው አፏ......

ደንግጬ እንቅልፌ ጠፍቶ ወዬ ወይ ምን ሆንሽ አልኩኝ........

ለሊት ሰባት ሰዓት ከምናምን የሷ የስልክ ጥሪ ነው ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ ሰላም ወንድሜ አብይ ግድ መምጣት አለብህ እስካሁን እዚህ ናት ሁል ጊዜም ከምገናኝበት ቤት......ያለው አስተናጋጅ ነው ስልኩን ተቀብሎ ያነጋገረኝ.......

በደንብ ማሽከርከር የማልችለው ልጅ ስከንፍ የሔድኩት......

እንደወረድኩ እርምጃዬን ፈጠን አድርጌ ከፊቴ የሚገጥሙኝን የሰው እንቅፋቶች እያለፍኩ አንድምንም አጠገቧ ደረስኩ.......

ስደርስ ብቻዋን በብዙ ቢራ ጠርሙሶች የውስኪ ጠርሙስ አንድ እጭር መለኪያ ብዙ ሎሚዎች ተከባለች........እጇን የጠረቤዛው መሃል ላይ አድርጋ ጠርሙሶቹ ከበዋታል በጧቿ ወፈር ያለ ሲጋራ ይዛለች ሳያት ደነገጥኩ...............

አንገቷን ከጠረቤዛው ላይ ቀና አድርጌ ምን ሆንሽ ምን ተፈጠረ አልኳት........ረጅም ፀጉሯ ፊቷን ሸፍኖታል እንደምንም ሰብስቤ ወደኃላ አድርጌ ፊቷን መጠራረግ ጀመርኩ........


ኖ አብዬ የሰከርኩ መስሎህ ነው እይደል እህ እህ ስቅ ይላታል......አልሰከርኩም

ማን ሰከረች አለ የኔዋ........ተነሽ በቃ አሁን ወደቤት እንሒድ እዛ እንነጋገራለን....ተነሺ


ደስዬ......እባክህ ሒሳብ አምጣልን አልኩት

አብዬ ሒሳብ ከፍላለች ብዙ ብር መልስም ነበረው ያዘው አለችኝ ይኽው አለኝ ደስዬ የኔ ምስኪን ሁሌም እሱ ነው የሚያስተናግደን እንደወንድማችን ነው.........

በቃ መልካም ያዘው ያዘው ላንተ ሲያንስህ ነው አልኩት ከልቤ ነው እንደዛ ያልኩት ሲበዛ መልካምና ጠንካራ ሰው ነው......

አልሔድም እንድናወራ ነው የምፈልገ እለችኝ

እሺ እሺ ቀስ ብለሽ አውሪ......ይኽው እቀመጣለሁ እናወራለን እሺ....

አው ጎበዝ ብላ አቀፈችኝ ልትወድቅ ነበር......ደግፌ ያዝኳት እንጂ....

አብዬ ቆንጆ አይደለሁም እንዴ.......?አለችኝ

ማ አንቺ በፈጣሪ እንዳንቺም ቆንጆ የለም ሁሉም የኔ በሆነች ብለው የሚመኙሽ ልጅ አይደለሽ እንዴ ይሔ ጠፍቶሽ ነው ቅን መልካም ደግ ሩህሩህ በሳል...ንግግሯ የተቆጠበ......ጥሩ መሪ የተከበርሽ......

እየዋሸኽኝ ነው.....😔🥺😔🥺


እንደማልዋሽ ታውቂያለሽ የምነግርሽ የሆንሽውን ነው.....

ይልቅ ዛሬ ምን ሆነሻል??

ስማኝማ አብዬ..........ብላ

.
.
.
ይቀጥል ይሆናል.............

በለሊት የተደረገ ጨዋታ...

@jahABP ነኝ አስተያየታችሁን አድርሱኝ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →