AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
ቤተክርስቲያን ውስጥ ካልተያዘችብኝ ማለቴ ሌላ ሰው ካልተቀመጠባት ሁሌም የምቀመጥበት ቦታ ላይ ፀሎቴን ጨርሼ ቁጭ ብያለሁ.............በነጠላዬ አፌን ሸፍዬ ከራሴ ጋር እያወራሁ ነው........
አንዱን ሳነሳ አንዱን ስጥል..... በአባቶች የትህትና ሰላምታ ስገረም ህፃናት ከልብ በሆነ ደስታ እየተሳሳቁ እየተሯሯጡ ሲጫወቱ ክፋትን አለማወቃቸው ይሆን እንዲህ ደስተኛ ያደረጋቸው ወይስ እዚህ ቦታ እንዲህ እንደሚደረግ ስላላወቁ ነው?? እራሴ እጠይቃለሁ........በባዶ እግራቸው ዣንጥላቸውን ከፍ አድርገው ይዘው እልልልልልልልልል እያሉ ፈጣሪን የሚያመሰግኑ እናት ድምፅ አነቃኝ::
ስልኬን አውጥቼ ሰዓቴን አየሁ ገና ነው የትም አልሔድም ደሞ ከዛ ሁካታ አለም እዚ የሰላሙ ቦታ ይሻለኛል ቤተክርስቲያን ለስንታችን ማኩረፊያ ናት ማረፊያ ናት እኮ በተለይ ለእንደኔ አይነቱ አልቃሻ ሰው:: ቤተክርስቲያንን የሰጠን አምላክ የተመሰገነ ይሁን:: ደሞ የጌታን ደም በዋንጫ ተቀብሎ ዓለም ላይ ረጭቶ ደሙ ባረፈበት ቦታ ሁሉ ቤተክርስትያን
ይታነፃል ያንን ያደረገ መልዐክ ቤት ውስጥ ነው ያለሁት ከተቀመጥኩባት ቦታዬ ፊት ለፊት ደሞ በሰዓሊ ዮሴፍ በአፍ የተሳለው ስነስዕሉ ይታይኛል ቅዱስ ዑራዔል የኛ እባት::
ይበርደኝ ጀመር ከሀሳቤ ስነቃ ነው ሀሳብ ውስጥ ስንሆን ብዙ ነገሮች አይሰሙንም ማለት ነው ነጠላዬን ተሸፋፈንኩ::
ፊት ለፊቴ ትንሽ ራቅ ብሎ ሁለት የሚያምሩ አበቦች ቀስ እያሉ እየተንሳፈፋ ወደ መሬት ወረዱ.......ከአንድ ዛፍ ላይ ነው የወረዱት ቀና ብዬ ዛፉን አየሁት በብዙ ተመሳሳይ አበቦች የደመቀ ነው::
እነዚዮቹ እንዴት ወደቁ?? በንፋሱ ሀይል ነው ወይስ?? ወፎች ለመቅሰም ብለው ነው የጣሏቸው??
ብቻ ወድቀዋል ብቻ ያምራሉ................
ዝም ብዬ አያቸዋለሁ ፀሀዯ አየሰፋች እየሰፋች ወደእነሱ ጋር ደረሰችና መሉ ለሙሉ ሸፈነቻቸው....
እኔ ፀሃይ አልወድም ውውውው ፀሀይ ከመታኝ እራስ ምታቴ ይነሳብኛል ለሊቱን ሙሉ እንቅልፍ የለኝም በጣም እታመማለሁ ያስለቅሰኛል.......ሁላ::
ከአበቦቹ ውበት የሆነ ነገር ሲጎል አየሁ የፀሀዯ ሙቀት እያጠወልጋቸው ነው ማለት ነው አልኩ ለራሴ ከአባታቸው(ከዛፋ) ሲለዩ ይሆን መድረቅ የጀመሩት?? ከነዛ ከሚያማምሩ አበቦች ተለይተው ሲመጡ ምን ተሰምቷቸው ይሆን??
ከዛም አንዱ አበባ አየተገለባበጠ ወደ ጥላው ተንቀሳቀሰ...........አንድኛው ደሞ እዛው ባለበት ነው ምን ይፈጠር ይሆን አልኩ ለራሴ.............
ወደ ጥላው የተንቀሳቀሰው አበባው ወደ ቀድሞው ውበቱ መመለስ ጀመረ.........ፀሀዩ ላይ ያለው ደሞ ከበፊቱ ይልቅ ውበቱን እያጣና እጠወለገ ነው::
ብዙ ሃሳቦች ወደ አእምሮዬ ማመላለስ ጀመርኩ....
ሆሆሆሆሆሆሆሆሆ
አበቦቹ እኛን መሰሉኝ ከፈጣሪያችን ተገንጥለን ወድቀናል ..........ለዛም ነው የባከን ህይወትን እያሳለፍን ኑሮአችንን ሁሉ አልሞላ ያለን ስራ አልሳካ ያለን ከሰዎች ጋር መግባባት ያቃተን ካለብን ሱስ አልላቀቅ ያልነው ክፋትን ማሰብ ማቆም ያልቻልነው እኔ ብቻ ነኝ ልክ የምንለው የኔ ጥቅም ካልተነካ ስለለሌላው ምን አገባኝ የምንለው ገንዘብ ካለ ሁሉም አለኝ የምንለው ሀጢያት የማይሰለቸን የኛ የሆነው የኛ ብቻ የሰው የሆነው የጋራ አድርነን የምናስበው ካለን ላይ ማካፈል የማንወደው ለእግዜርም የሚገባውን የማንሰጠው ያለኔ ምን ልታደርግ አትችሉም ብሎ በቃሉ ነግሮን ህይወትን ከሱ ውጪ ለመኖር ዋናውን የከሰረ ነጋዴ ሆነን የምንቅበዘበዝ ሁለቱ አበቦች እኛ ነን::
እዚች ወከባ የበዛባት ምድር ላይ የራሱን ሁሉም ጥቅም የሚያስቀድምባት ምድር ላይ ወድቀን መተናል አሁን የህይወት ትልቁ ጥያቄ መውደቁ አይደለምሰው ነንና እንወድቃለን ዋናው ነገር አሁን ካለንበት ተንቀሳቅሰናል ወይ ነው?? እውነት ምትለውን ለማግኝት ተንቀሳቅሰሃል?? ከከሰርክበት ለመውጣት ተንቀሳቅሰሃል?? ካለብህ ሱስ ለመላቀቅ ተንቀሳቅሰሃል?? ራስ ወዳድነትህን ለማቆም ተንቀሳቅሰሃል?? ችግርን ከመጋፈጥ ብለህ ነገ መልሶ እንደሚመጣልህ እያወክ እየተደበክ ለማምለጥ የምትሞክረው ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ተንቀሳቅሰሃል ወይ?? የሌሎች መሳሳቻ ላለመሆን ተንቀሳቅሰሃል?? ትምህርትህን ካቆምክበት ለመቀጠል ተንቀሳቅሰሃል?? ለውድቀትህ መጀመሪያ ሌሎችን ሳይሆን እራስህን ለመውቀስ የቀረኝ ነገርአለ በለህ እሱን ለማወቅ ተንቀሳቅሰሃል?? አላማዬ ብለህ ላስቀመጥከው እዛ ጋር ለመድረስ ተንቀሳቅሰሃል??የተውካት ባለቤትህን የጣልካቸው ልጆችህን ለመሰብሰብ ተንቀሳቅሰሃል በውሸት የምትገነባውን ለማቆም ተንቀሳቅስሃል.........ከሁሉም በላይ ድሞ ወደ ፈጣሪስ ለመቅረብ ተንቀሳቅሰሃል???
መዳጄ እባክህ ተንቀሳቀስ ያለወውደቅን ያህል ወድቆ መነሳት ክብር ነውና ከመድረቅና ከመጠውለግ በፊ ወደ ጥላው ተንቀሳቀስ አንድ ቦታ አትቁም የረጋ ውሃ ስለማይንቀሳቀስ ይሸታል አንተም ሰዎች እንዳይፀየፋህ አንድ ቦታ አትቁም..... "አትምረጥ አለማወቅን አውቀህ አትጨፍን እይ ውደቅን"ወደ አምላክህ ተጠጋ የፈለገው እንደሚያገኝው ተናግሯልና.............::
ይህን እያሰብኩ አንዲት ቆንጅዬ ህፃን ባጠገቤ አልፋ....ጥላው ላይ ያለውን ውበቱ የተመለሰውን አበባ አንሳችው ወደፊት ስትራመድደሞ የጠወለገውን አበባ እረግጣው ሔደች.....አየህ ካለህበት ካልተንቀሳቀስክ ሰውች ረግጠውህ ለማለፍ ይገደዳሉ.....ልጅቷን በአይኖቼ ተከተልኳት እይሮጠች ነው የምትሔደው ምትወድቅ ትመስላለች አሳቀቀችኝ እሮጣ አባቷ ጋር ስትደርስ የያዘችውን እበባ ለአባቷ አሳይችው እሱም በፍቅር አቀፋትና እበባውን ተቀብሎ ፀጉሯ ላይ ሰካላት........እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል ነው........አየህ ካለህበት ወደ ለምለሙ ወደ መልካሙ ትንሽ ፈቀቅ ስትል እድልህ አናት ላይ ወቶ መቀመጥ ይሆናል::
ወዳጄ እባክህ ተንቀሳቀስ ወደፈጣሪ ተጠጋ እሱ ቸር ነው ሁሌም ሊያቅፈን ይፈልግይል አንተ ማድረግ ያለብህን ካደረክ ፈጣሪ ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል::
ደሞ ይህን ለራስህ ንገረው ፈጣሪህን የከሰርክበት ማንኛውም ድል ሽንፈት ነው::
ፈጣሪ ከሁላችን ጋር ይሁን::
ይህ ገጠመኜ ለሁላችን መማሪያ ይሆናል እላለሁ ወደፊት ሰፋ ባለ ፅሁፍ ታገኙት ይሆናል ይህ ለቴሌግራም እንዲመች ተደርጎ እንደትፃፈ ልብ ይሏል::
አብይ የማርያምልጅ ነኝ( @jahABP ) አስተያየታችሁን እድርሱኝ::
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #2189
665