የተሸከሙት እቃ ሳይከብዳቸው ከሰው ጋር አውርቼ እስክጨርስ ጠብቀው አብዬ ብለው ጠርተው እጅህን ተሻለህ ወይ ብለው ጠየቁኝ😔😔 ልቤ ነው የተነካው አመመኝ ብዬ ነግሬያቸውም እኮ አይደለም ከትንሽ ቀን በፊት እጄን አሞኝ ስለነበር ለየሰፈራችን ወጌሻ በመንገድ ሲያልፍ እያሳየሁት አይተውኝ ነበር::
እና በሙቅ ውሃ ጨው አድርጌ እንድታጠብ በቫዝሊን አድርጌ እንድታሽ እናታዊ ምክራቸውን ለግሰውኝ ነበር::
ይኽው ዛሬ የኔ ነገር አሳስቧቸው ቆመው ጠብቀው ደህንነቴን ጠየቁኝ😔🥲🥲😢😢 እናንተ መልካም ሰዎች እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቃችሁ ረጅም እድሜን ከጤና ጋር ያድልልኝ::
ውብ ሰዎች አሉ ብያችሁ አልነበር🥰😍🥰😍😘🙏🙏🙏🙏
አብይ የማርያም ልጅ ነኝ @jahABP
መልካም ምሽት ይሁንልን
Post #2163
543