ባለትዳር ጟደኞቼን የተወሰነች ክፍተት አየሁኝና ማናገር ነበረብኝ......መገሰፅ ሳይሆን የወንድምነቴን እንዲ ቢሆን እንዲ ነው እንዲ ቢደረግ መልካም ይመስለኛል ለማለት ፈልጌ ነበር.........እና ይህን የወጣት አፌ ከመጥገን ይልቅ እንዳይሰብር ብዬ ..........ንግግሬ የተገታ ይሆን ዘንድ የተወሰኑ መንፈሳዊ መፅሐፍትን አገላብጬ ነበር::
በጣም ጥሩ ምክርና መልዕክትን እግኝቼባቸዋለሁ የእውነት ነው የምላችሁ የነሱ ዛሬ ብቻ ሳይሆን የኔ ነገዬን እንዳስብ ሆኛለሁ ለካ #ባልነት ከምናስበው በላይ ትልቅ ሀላፊነት ነው:: በእውነት ለባልነት ገና ብዙ ሚቀሩን ነገሮች አሉ ራሴን ታዝቤያለሁ::
#ሚስትነትም እንደዛው ትዳር ላይ እንዲሁ እንደ ቀላል ሚታይ ምንም ነገር የለም.......::
ካነበብኩትና እንደኔ ትንሽዬ የዕውቀት ደረጃ የተረዳኃትን ለንባብ እንዲመች አድርጌ አቀርበዋለሁ::
አብይ የማርያም ልጅ ነኝ:: (@jahABP ) ነኝ
ክፉውን እሳንሶ መልካሙን አጉልቶ የሚያሳይ ዐይን ያድለን::
መልካም ጊዜ ተመኝሁ
እንደሁልጊዜው ጠብቁኝማ👣🦶🏿👣🦶🏿
Post #2155
599