AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
#የአፋልጉኝ_ማስታወቂያ
ምሳ ሰዓት ካለፈ በኃላ ስራ ቦታዬ ላይ መፅሃፍ እያነበብኩ ድንገት ወንድሜ እባክህን ውሃ ታጠጣኛለህ የሚል ድምፅ ከንባቤ ገታኝ...
እሺ በደስታ አልኩትና ከተቀመጥኩበት ተነስቼ በጆግ ውሃና ብርጭቆ ይዜ ተመለስኩ
ኒኬል የለህም ብርጭቆህን እንዳላቆሽሽብህ አለኝ የዛኔ ነው በህይወት ውጣውረድ ጉስቁል ያለ ሰው መሆኑን ያስተዋልኩት::
ኧረ ችግር የለውም ወንድሜ ቢቆሽሽ ታዲያ ይታጠብ የለ እንዴ ጠጣ ጠጣ ችግር የለም ሃሳብ አይግባህ አልኩት::
በማፈር ስሜት ቢሆንም በደንብ ጠጣ እንደደከመው ያስታውቃል😔😔 ምግብ ይቅረብልህ ትበላለህ አልኩት☹️
ማስቸገር ባይሆንብኝ ብበላ ደስ ነው ሚለኝ አለኝ::
እሺ ቁጭ በል ምንም ችግር የለም ምን ይምጣልህ ስል ከትንሽዬ ምግብ ቤቴ ውስጥ ያሉትን መምግብ ዝርዝር ነገርኩት........
እሱም አንተ ደስ ያለህን አምጣልኝ መምረጥ አያምርብኝም አለኝና ፈገግ አለ
አሪፍ ያልኩትን አዘዝኩለት አቀራርቤለት ወደ መፅሃፌ ተመለስኩ
መፅሐፍ ማንበብ ጥሩ ነው ጥሩ ሰው እንድትሆን ምክንያት ይሆንሃል ያሰው የደረሰብትን እውቀትና የህይወት ተሞክሮም ታገኝበታለህ ታዲያ አንተ ከራስህ ህይወት ጋር እስማምተህ ስትጠቀምበት የተሟላ ሰው እንድትሆን ያግዝሃል አለኝ
አው ልክ ነህ ከመፅሐፎች ያገኝሁት እውቀት አያሌ ነው እራሴን እንዳገኝ ጥሩ ሰው እንድሆን አድርገውኛል::
በርታ እንዳትሰንፍ አለኝ
በሚገባ እሺ እሺ አልኩት
.
.
.
ምግቡን በልቶ ጨርሶ ሊሰናበትኝ ሲነሳ ታውቃለህ ከቦሌ መድሃኒዓለም እዚ አንተ ጋር እስክደርስ ድረስ ድረስ የገኝኃቸው ምግብ ቤቶች ሁሉ ተመላሽ ምግብ ካላቸው ስጠይቅ ነው የመጣሁት አንድም ቤት ግን አላገኝሁም በጣም እርቦኝ ነበር በጣም ትላንት ማታ የበላሁ ነኝ እዚ አንተ ጋር እራሱ ውሃ የጠየኩህ እነዛ ትልቅ ቤቶች ያላገኝሁ እዚህማ አላገኝም ብዬ ነው አንተ ግን ውስጤን ተረዳህልኝ አወከኝ አበላኽኝ አጠገብከኝ ፀሃዩንም እንደምታየው ነው በጣም አድክሞኝ ነበር ትንሽ ብቆይ ምወድቅ ይመስለኝ ነበር አመሰግንሃለሁ ጠግቤያለሁ እግዚአብሔር አምላክ የሚያጠግብህን ሀብት እሱ ይስጥህ የምትሰጠው አትጣ......ብቻ ብዙ ብዙ ነገሮችን መረቀኝ እኔም አሜን ብዬ ተቀበልኩ::
እንዲህ ነው ትውውቃችን የጀመረው........
ከዛ ጊዜ ጀምሮ ከአንድ አመት በላይ ሁሌ አርብ አርብ ይመጣል አርብ ባይመጣ እንኳ ዕሁድ ይመጣል የሚፈልገውንም እንደምርጫው ይመግባል እንጫወታለን እንስቃለን........እኔ ባልኖር እንኳን በነፃነት ይመገብ ዘንድ ሰራተኞቹን አስተዋውቄው ስለነበር ባልኖርም እንደቤቱ ይሰማው ነበር እኔም በአቅሜ ማድረግ ምችለውን እያደረኩ ከሰዎችም እየጠየኩ የሚያስፈልገውን ለምስጠት እሞክር ነበር::
ሲሰናበትኝም ሁሌም ድምፁን ከፍ አድርጎ ነበር እኔም ምርቃቱን አሜን ብዬ እቀበላለሁ....
ብታዩ ሁሌም እጠብቀው ነበር ሲመጣ በጣም ነበር ደስ የሚለኝ ለኔ በረከቴ ነበር ታዲያ አሁን ይኽው ከተገናኝን ቤት ከመጣ ድፍን ሁለት ወር አለፈን በጣም አዝኛለሁ በጣም አዝኛለህ ስልክ የለው አልደውልለት ሚያድረውም ማደሪያ ቤቶች ስለሆን የት ብዬ ልፈልገው 😢😢🥺🥺 ምን ሆኖ ይሆን ብዬ እየተጨነኩ ነው ብዙ አርብና እሁዶች አለፉ ምን ሆኖ ይሆን😢😩🤔
አብዬ የእውነት ነው የምልህ ወንድሜ ስትለኝ የሚሰማኝን ደስታ ልነግርኽ አልችልም የምትለው ድምፁ አሁንም ጆሮዬ ስር ያቃጭልብኛል😢😢😩
ወንድሜ የት ይሆን ያለኽው??? እባክህ ና
ስም ፎቶ አድራሻ የሌለውግራ የገባው የአፋልጉኝ ማስታወቂያ..........
እንደምትመጣ ተስፋ አደርጋለሁ
ሀላችሁም ፀልዩልኝ.......🙏🙏🙏
ትልቅ ነገር አደረክ እንዳትሉኝ ምክንያቱም
ውሻን በወርቅ ጫማ ውሃ ያጠጣች ድንቅ አዛኝ እሩህሩህ እናት ወላዲተ አምላክ ናት ትምህርት ቤቴ::
ድንኳን በከተማ ዘርግቶ እንግዳን ሳያበላ እህል የማይቀምሰው የሁላችን አባት የአብርሃም ልጅ ነኝ::
በእነሱ አይን እንጂ በሰውኛ አይን አትዩኝ በእነሱ ስታይ ስራዬ ምንም ነውና.....
@jahABP ነኝ አስተያየታችሁን አድርሱኝ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #2141
615