የሆነ ቀን ስለ ልክ መሆን voice እየተቀዳሁ ነበር ሰው ገባብኝና አቋረጥከት::
ልክ መሆን ምንድነው?? እኛ ልክ ነው ብለን ያሰብነው - ልክ መሆኑ በምንድነው ሚመዘነው??
እኔ ልክ ነኝ ሌሎች ልክ አይደሉም ማለት ነው??
እነሱ ልክ ናቸው ማለት እኔ ተሳስቻለሁ ማለት ነው??
ልክ አለመሆኔን ሲያስረዱኝ ለምን ለመቀበል ከበደኝ?? እኔ የእነሱን ልክ አለመሆን መሳሳት ስነግራቸው ለመቀበል እንደተቸገሩት ሁሉ ነው??
ወይስ ማድረግ አትችይም ወደሚለው ድምዳሜ ላይ ደርሰው ለኔ ሊወስኑልኝ እየሞከሩ ነው??
ሃሃሃሃ እንዳያስቡት
እቆይና ደሞ ውሳኔ ምወስንበት ደረጃ ላይ ነኝ እንዴ??? አስባለሁ........እኔንጃ ነኝም አይደለሁምም ሃሃሃሃሃ
ደሞ ተቆጣጥረው ሚያድኑኝ አይመስሉም..........
በመሃላችን ዝምታ ነገሰ........
ምን ትላለህ አልችኝ.................
ዝም አልኳት.......
ኡፍፍፍ............
እኔም ብሆን የምልሽ እንደነሱ ነው ግን እይታዬን አስተካክዬ ነገሮችን አንግላቸውን ቀይሬ ነው አሳምኜ ሀሳብሽን እንድትቀይሪ ማደርግሽ:: አንቺ ልክ አይደለሽም አላልኩም አልልሽም ግን እኔ ያሰብኩብት መንገድ ያንቺን ልክ አለመሆንጥርት አድርጎ ያሳይሻል ባይ ነኝ::
ልክ ለመሆኑ ላለመሆኑ ሳይሆን የአሁኑ ፍላጎቴ ነው በምትይው ውሳኔሽ ባንቺ ህይወት ላይ ምን ጥሩነገር ምንስ መጥፎ ነገር ያመጣል የቱ ጎኑ ይሰፋል ነው::
እንደቤተሰብስ ምን ያመጣብናል???
ወጣት ልጅ ነሽ ቆንጅዬ ሁሉም የኔ በሆነች ብለው የሚመኙሽ......... ልጅ ነሽ.........
ስልክ ተደወለልኝና ንግግሬን ገታሁ..........
#ከሷ_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ
በቅርብ ቀን
ጠብቁኝማ🦶🏿👣🦶🏿👣
አብይ የማርያም ልጅ ነኝ @jahABP
Post #2131
601