TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #2058 803
።። ።። AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ።። ።።


#ገፍተው_ገፍተው

ቅቤና ማር ተከራከሩ ይባላል..... ማርም ተናገረች "የምጣፍጠው እኔ አናት ላይ የምትወጪው አንቺ ነሽ ለምንድነው? አለቻት:: ቅቤም "እኔም ወድጄ አይደለም ገፍተው ገፍተው ነው አናት ላይ ያወጡኘ አለች ይባላል፡፡

እግዚአብሔር ሁሉም ሎሌው ነው፡፡ በክፉዎች ሳይቀር ይሰራል፡፡ ወዳሰበልን የሚያደርሰን እየገፋ ነው፡፡

ካልተገፋን ያለንበትን ትንሽ ቦታ ተላምደን እንኖራለን፡፡

እርሱ በደጎች አይገፋንም ደጎች መግፋት ባህሪያቸው አይደለምና፡፡ ክፉዎች ግን ቅድስናም ይሉኘታም የላቸውምና በእነርሱ ይገፋናል፡፡ እነርሱ የሚያውቁት ወደ ገደል እንደሚገፉን ነው ሳያውቁት ግን ወደተራራ ይገፉናል፡፡

ጠላቶች የነፃ ሰረገላዎቻችን ናቸው፡፡ ከማንፈልግበት ቦታ እየገፉ ወደምንፈልግበት ቦታ ያደርሱናል፡፡ በእውነት ጌታ ሆይ ጠላቶቻችንን ባርክልን፡፡ እነርሱ ባይኖሩ ስራው አይበዛልንም ነበር፡፡

የተገፉ ሁሉ ከፍ ሲሉ እንጂ ዝቅ ሲሉ አይተን አናውቅም፡፡ ገፊዎች ሲገፉን ከእኛ የክፋት መንደር ምን ትሰራላቹ? አለፍ በሉ እየያሉን ነው፡፡ ጠላቶች ሀሰተኛ ወዳጅቻችንን ወስደው እውነተኛ ወዳጆችን ያስቀሩልናል፡፡

ክፉዎች ጥሩ ማጣሪያዎቻችን ናቸው፡፡ተረስተን የምንኖረውን እነርሱ ያሳውቁናል በነፃ ማስታወቂያ ይሰሩልናል፡፡
ሰዎች ስማችንን የሚያነሱት በሁለት ነገር ነው....የመጀመርያው ስለሚወዱን ስላስደሰትናቸው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ስለሚጠሉንና ስላስጨነቅናቸው ነው፡፡

እንዲሁ እርዕስ መሆን አይገኘም፡፡
የአትርሱኘ ሳንከፍል ላስታወሱን በረከት ይሁን፡፡ ዮሴፍ ባይገፋ ጎበዝ እረኛ ይሆን ነበር በመገፋቱ ግን የግብፅ ጠቅላይሚኒስትር ሆነ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን ከኢየሩሳሌም ሊያጠፉ ፈልገው ገደሉት በሞቱ ግን በዓለም ሁሉ አበራ

#ጠላት_ያውቃል_እንላለን_እንደጠላት_ግ_አላዋቂ_የለም፡፡

ጠላት ሰፈር እየቀማ አለምን ያወርሳል፡፡
ሰው ማፍረስ ይችል ይሆናል እግዚአብሔር ደግሞ ማስነሳት ይችላል፡፡

መገፋት ጥሩ ነው እጅግም ሳይወድቁ፣
የተገፋት ቆመው የገፉት ወደቁ፡፡

እንደ ማር የሚጣፍጡት ወደላይ አይወጡም የተገፉት ግን ወደላይ ይወጣሉ፡፡

በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ ታሪኳን የምናገኘው ሴት ጠላቶቿ ገፍተው ገፍተው ያደረሷት ጌታ ጋር ነው፡፡ ኃጢያት ይቅር ወደ ሚለውና በሰላም ድምፅ ወደሚሸኘው ጌታ አቀረቧት፡፡ ተከሳሿ በነፃ ስትመለስ ከሳሾች ግን የእርሷንም አበሳ ተሸክመው ተመለሱ፡፡

ልዑል ራስ ካሳ ኃይሉ የዙፋኑ እንባ ጠባቂ ነበሩ፡፡ መሳፍንትም መኳንንትም ወደእሳቸው አቤት ይላሉ፡፡ አንዱ መስፍንም:- "ልዑል ሆይ ተገፍቻለሁ ተገፍቻለሁ የሚገባኘን ሹመት አላገኘሁም አላቸው"፡፡ እርሳቸውም ሰሙና:- "ልክስክስ ገፊ ቢገፋህ እንጂ ደህና ገፊ ቢገፋህ ኖሮማ ታድግ ነበር አሉት" ይባላል፡፡

በእውነት ጌታ ሆይ ገፊዎቻችንን ጠላቶቻችንን ባርክልን እነርሱ እንዳይነቅፉን ስንጠነቀቅ የቅድስናን መንገድ የቅድስናን ሕይወት ተለማምደነዋልና፡፡

#ገፊ_ያሳድጋል

አስተያየታቸሁን @jahABP 😍🙏😍

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →