ዕሁድን ያሳለፍኩት በ #MA_TRIP በተዘጋጀው በአብያታ ሻላ ሀይቆች ጉዞ ላይ ነበር፡፡ በጣም ደስ የሚል አስደሳች ጊዜ አሳልፈናል ሁላችሁንም አመሰግናለሁ😍🙏
ሰጎን በዓይኔ ስመለከት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው😱😱😱😱
የተፈጥሮ መስህቦቻችን ላይ ምንም እንዳልሰራንባቸው ተገንዝቤያለሁ እንዴት ያን የሚያህል 800 ምናምን ስኩዌር ኪ.ሜ ላይ አንድ ዘመናዊነቱን የጠበቀ lodge አይኖርም ቱሪስት ሲመጣ ምን ሊመገብ ነው የትስ ሊያርፍ ነው🤔🤔🤔 እውነቴን ነው የምላችሁ እንስሳቶቹ ሊያመልጡ ቢሞክሩ የሚያቆማቸው ደና አድርጎ የተሰራ አጥር እንኳን የለውም ለመሰረቅም ለመገደልም ቅርብ ናቸው እስካሁንም የቆዩት በፈጣሪ ስራ ነው ብዬ ነው ማስበው ሰውንስ ሊያጠቁ ቢሞክሩ ፓርኩ የራሱ የሆነ የመከላከያ መሳሪያ ያለውም ያሰለጠናቸው ሰራተኞች ህክምና መስጫም ያለ አይመስለኘም ምክንያቱም አስጎብኚያችን ያንን አልነገረንም፡፡
መንግስት ሆይ እባክህ ሌሎቹ ፓርኮች ለአይን እንዲስቡ አድርገህ ጥሩ የቱሪስት መናኸሪያ እንዳደረከው ይህን ድንቅ ቦታ ተመልከትልን ብዙ ነገር መሰራት ይችላልና፡፡
እኔ በበኩሌ ደስም ቢለኘም ግን ፍርሃትም ነበረብኘ የሆነ ነገር ብንሆንስ የሚል🤷♂🤦♂🤷♂
በዚህ ጉዞ ያነሳኀቸውን ገራሚ ፎቶዎች ጀባ ልበላችሁ......
በቀጣይ ማለትም ከ15 ቀን በኀላ ጉዞው ስላለ አብራችሁን እንድትመጡ ስንጋብዝ በደስታ ነው፡፡ ጥሩ ጊዜን እናሳልፋለን፡፡
1.......2.......3
@jahABP ነኘ 😍😊🙏
👣👣👣👣👣👣👣👣
Post #1951
642
