TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #1943 758
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#መስቀል

"መስቀል የሚለው በፊደል ሲተነተን

መ-መከራ ስ-ስቃይ ቀ-ቀራንዮ ል-ልቅሶ ነው፡፡

ጌታችን ስለኛ የመረጠው በመስቀል ላይ መሞትን ነው፡፡ እርሱ ወንጀለኛ ካልተባለ እኛ ፃድቃን ልንሆን አንችልም፡፡ እርሱ እርግማናችንን ካልተቀበለ እኛ በረከትን መውረስ አንችልም፡፡ "እኛን ከፃድቃን ጋር ሊደምረን እርሱ ከበደለኞች ጋር ተቆጠረ" ጌታን በመስቀል ላዬ በሁለት ሽፍቶች መካከል ስናየው ይደንቃል ጻድቃንን የሚያፀድቀው እንደ ወንጀለኛ መቆጠሩ ሱራፌልና ኪሩቤል ፣ ሚካኤልና ገብርኤል ቅዱሳን መላዕክት ቅዱሳን ፃድቃን ሰማዕታት በፊቱ የሚንቀጠቀጡለት በሽፍቶች መካከል መሰቀሉ ከአእምሮ በላይ ነው፡፡

መስቀል በቤተ አህዛብ ካለው የወንጀለኛነት መቅጫነት ከቤተ አይሁድ ከነበረው የርግማን ምልክትነት ወጥቶ የክርስቲያን ዓለም ሰንደቅ ዓላማ ወይም ምልክት ሆኗል፡፡ በእያንዳንዱ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጉልላት ላይ የመስቀል ምልክት ይታያል፡፡

የመስቀሉምለክት ስናይም ከተራ መሰብሰቢያ አዳራሽ የተለየ ቤት እንደሆነ እንረዳለን፡፡ መስቀል በአገራችን ሴትችና ወንዶች በግንባራቸው ላይ የሚነቀሱት በልብሳቸው ላይ የሚጠልፉት ማጌጫ ነው፡፡ በምልክቱ ብቻ በሚያስገድልበት አለም በግንባር ላይ በማድረግ በክርስትና መኩራትን ዋጋ ለመክፈል መጨከንን ያመላክታል፡፡

መስቀል ቅርፁ ብቻውን የሚያስተምረን ነገር አለ፡፡ የሰው ተፈጥሮ በራሱ መስቀል ቅርፅ ነው፡፡ ሰው ሁለት እጆቹን ሲዘረጋ የመስቀል ቅርፅ ይመጣል፡፡ የሰውም መዳን የተፈፀመው በመስቀል ላይ ጌታ በከፈለው ዋጋ ነው፡፡

መስቀል በፊደላቴ ተ የሚለውን ፊደል ይወክላል፡፡ #ተከፍሏል ማለት ነው፡፡፡ የሞት ዕዳችን በክርስቶስ መከፈሉን ያመላክታል፡፡ አደጋ የሚበዛው በመስቀለኛ መንገድ ላይ ነው፡፡ እንዲሁም የመስቀሉ ሕይወትብዙ ፈተና ያለበት ነው፡፡

እውነተኛው ክርስቶስ መስቀል እልባ ሳይሆን ባለመስቀል ነው፡፡ ይህ ማለት ክርስቶስ የመጣው ለምቾቱ ሳይሆን ለመሞት ነው፡፡ በእርሱ ስም የመጡት ሐሰተኛ ክርስቶሶች ግን ለመደላደል መጥተዋል፡፡

መስቀል ጥልቅ ትርጉሙ መንፈሳዊነት ነው፡፡

መስቀል ጥልቅ ትርጉም ያለው ከሥነ መለኮት ቃላትም አንዱ ነው መስቀል ከሚታየው ይልቅ የሚታሰበው ትርጉሙ በመንፈሳዊ አዕምሮ ብቻ የሚደረስበት ነው፡፡
ክርስቲያኖች መስቀል ብለን ስንናገር ስለሚታየን ቅርፅ ተነጋግረን በዚያ ረክተን የምንቀመጥ አይደለንም፡፡

ጌታችን ለሞተው ፍጥረት ሕይወት የሰጠው በእርግማን ለታሰሩት በረከትን የናኘው በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ነው፡፡ከአዳም የወረስነውን መርገም እየጎረፈ ትውልዶችን ሁሉ ያጠፋው ዕዳ ገደብ ያገኘውበክርስቶስ ሞት ነው፡፡

ክርስቶስ በመስቀል ላይ ባይሞትና ሞትን ባይገድበው ኖሮ የአዳም ርግማን እስከዛሬ የመፍሰስ አቅም ነበረው፡፡

የመስቀል ምስጢር እስካሁን አልተዘለቀም መስቀል ሰላምን እርቅን ህብረትን የሚያመላክት ነው፡፡ ልደት ሁሉ ምጥ ይቀድመዋል ያለምጥ ልደት የለም ሕይወት እንዲወለድ ቤተክርስቲያን እንድትወለድ ክርስቶስ በመስቀል ላይ አምጧል፡፡"

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ

@jahABP ነኘ 😊🙏😊



@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →