TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #1940 1.02K
#ከቦሌ_ጫፍ_እስከአራት_ኪሎ

እኔ:- ይሄ ሁሉ ያስቃል........

እሷ፡- እህ እህ ቂቂቂቂቂ አዎ በጣም የምር

እኔ:- የደስታሽ ምክንያት በመሆኔ ደስ ብሎኛል፡፡

እሷ:- በእውነት ከልብ አመሰግናለሁ

እኔ:- ኧረ እንዲች ብለሽ እንዳታስቢ ውድ

እሷ:- በነገራችን ላይ ለምንድነው ለአብዛኞቻችን ደስታን የሚሰጡን ሰዎች ከአጠገባችን ቶሎ የሚርቁን😔😔 የምሬን ነው ምልህ አንደ ሰው አምነኸው አንድም ሳታስቀር ካንተ የሚያስፈልገውን ሁሉን ሰጥተኸው እሱ ግን አንተን ይጎዳኻል🤦‍♀🙇‍♀
ለምን???

እኔ:- እሷ እያወራቸሸ ነው እኔ በግማሽ ልቤ ነው ምሰማት አንድ ሰው ሲስቅም ሲያዝንም ያምራል እንዴ ፈጣሪማ ያዳላል... ለምን እንዲህ ልትል ቻለች ለምን ብሶቷን ልትረገረኘ ፈለገች?/ ተጎድታለቼ ማለት ነው😔😔😔😔 ያወራችው ብዙ ቢሆንም የሰማሁትን ለመመለስ ያህል

አዎ እኔም ግራ ይገባኛል አንዳንድ ሰዎች እኛ ጋር ያላቸው ቦታ አይገባቸውም ለዛም ይመስለኛል የምሬን ነው ፍቅራችንን እንደ ቀላል ነገር ያዩታል ደግሞ እኮ የቅርብ ሰዎች በምንላቸው ይብሳል፡፡

እሷ:- እውነትህን ነው እኔንማ ስንቴ ሰበሩኘ🙇‍♀

አይዞሽ ውድ ሰዎች ስንባል ከባድ ፍጥረቶች ነን......አንቺ መጠንከር ነው ያለብሽ እንጂ ሁሉም ሰው እንዳንቺ ሊወድሽ አይችልም አንቺ እንደምትሆኚለት ሩቡን አይሆንልሽም፡፡
ይህን አስታውሺ ሰዎች ሁሌም ሒያጅ ናቸው ዋናው ነገር ምመክርሽ አንቺ በሰዎች ሳይሆን መደገፍ ያለብሽ በእግዚአብሔር ነው ያለበለዚያ እንዳልሽው የመጣው ሁሉ ሰብሮሽ ነው የሚሔደው፡፡

እሷ:- ልክ ነህ አሁን እየገባኘ ያለ ነገር ያ ነው ታቃለህ ሀይማኖት ላይ ደካማ ነኘ(ፈገግ አለች) ግን ያለ እግዚአብሔር ማንም የለኘም ያን እየተረዳሁ ነው ስንቴ ቤት ዘግቼ አለቀስኩ ስንት ዓመት ሱስ ውስጥ ተዘፈኩ ስንት ዓመት ፈጣሪን አስቀየምኩት መሰለህ ስንት ማድረግ የሌሉብኘን ነገሮች አደረኩ መሰለህ ግን ሁሉም ሲሰሸኘ የኔ ያልኳቸው ሲርቁኘ እግዚአብሔር ግን ሁሌም ከኔ ጋር ነበር በነዛ ጊዜያቶች ሁላ ከስንት ጉድ አውጥቶኛል መሰለህ ይህን ያስተዋልኩት ግን አሁን ላይ እሱ ለኔ ድንቅ ነበር #ውዴ_የኔ_ነው_እኔም የሱ ነኘ በማንነቴ አይርቀኘምና

እኔ:- አዎ ውድ እግዚአብሔር በማንነታችን አለመራቁ ሁሌም የሚገርመኘ ነገር ነው ታውቂያለሽ እግዚአብሔር ታላቅ የተባለው ከታላላቆቹ ጋር ስለሆነ አይደለም ታናናሾቹን ስላልናቀ ነው፡፡ እሱ አይተወንም ወደሱ እንድንመለስ ብዙ ይታገሰናል፡፡

እሷ:- ልክ ነህ እኔንማ በብዙ ታግሶኛል፡፡

.............ዝምታ...........ሹፌሩ መንገዱ በመዘጋጋቱ ያማርራል ይሳደባል መሪውን በየደቂቃው ይደበድባል....... ሆድ የባሰው መኪና መሪው አልንቀሳቀስም እንዳይል ፈራሁ ረዳቱ ሰው ለማስገባት እየጮኸ ይጣራል እኛም ከገባን በኀላ ሆኖ እንጂ....በእግር አይቀልም.........ውረድ ብባል እሺ ምል አይመስልም😜 ተሳፋሪው ምሬቱ ከፊቱ ይታወቃል የጠዋቷ ፀሀይም ከመብዛቷ ከመናፈቅ አልፋ የዛሬዋ ፀሀይ ደሞ ምንድነው በጠዋቱ እንዲ ማቃጠል ይላሉ በጥግ የተቀመጡ ጠና ያሉ ሰውዬ
ከፊታችን ያሉ ወንበሩ ያልበቃቸው ወፍራም ሴትዮ ትልቅ መነፅራቸውን አውልቀው አነስ ያለች ሻንጣ ከምታክል ቦርሳቸው ውስጥ ወፈር ያለ ወረቀት አውጥተው ወደ ሰውነታቸው አስጠግተው ያራግባሉ መስኮቶቹ ስለተከፋፈቱ ከውጪ ያሉት መኪኖች የጡሩንባ ድምፅ ለጆሮ ይረብሻል.....

እኔ:- ይቅርታ አንድ ጥያቄ መጠየቅ ይቻላል አልኳት

እሷ:- በመስኮት በኩል ወደ ውጪ እያየች ጭልጥ ካለችበት ሀሳብ ብንን ብላ ፊቷን የሸፈነውን ፀጉራን በእጆቿ....(ወይኔ ጣቶቿ 😍😍😍 በማስመሪያ ተሰምረው የተቀመጡ ነው የሚመስለው በዛ ላይ ያደረገችው የእጅ ጌጥ ከጠዋቷ ፀሀይ ጋር ተዳምሮ ፀሀይን የጨበጠች አስመስሏታል፡፡) ድሮም እጅና እግር ድክመቶቼ ናቸው፡፡ በእጆቿ ከፊቷ ላይ አንስታ sure ይቻላል አለችኘ......

እኔ:- ዕሁድ የምሔድበት መንፈሳዊ ጉዞ አለ እና መልካም ፈቃድሽ ከሆነ ከቻልሽ ቀጠሮ ከሌለብሽ አብረን ብንሔድ ደስ ይለኛል አያሌ መንፈሳዊ ነገሮችን ምታገኚበት ይመስለኛል ሴት ጓደኞቻችን ስላሉ ምንም የሚያስፈራሽ ነገር የለውም ልብስ ከፈለግሽ እንዲያመጡ እነግራቸዋለሁ እ ምን ይመስልሻል 😊😊😊 እ እሺ ብትይ ደስ ይለኛል(ለምንድነው ይሔን ሁሉ የምዘባርቀው ግን ምን ነካኘ🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂🤷‍♂🤷‍♂🤷‍♂🤷‍♂ አብያ)

እሷ:- እእእ....እእእእ.........


ይቀጥላል.....👣👣👣👣

@jahABP ነኘ መልካም ምሽት

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →