TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #1937 1.56K
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#እናመሰግንህ_ዘንድ_ምክንያታችን_ብዙ_ነው፡፡


በመኖር ያተረፍኩህ ሀብት ጥሪቴ ሁል ጊዜ ያገኘሁህ ከፍታዬ የድህነት ጎጆዬ መጨመር መጉደል የሌለብህ የዓይኔ ማረፊያ የልቤ ተስፋ አመሰግንሃለሁ፡፡ ወዳጅ የማይሰጠውን የሰጠኸኘ ከእናት ጓዳ የማይገኘውን ሰላም የናኘህልኘ አንተ ሀገሬ አመሰግንሃለሁ፡፡

የልቤን የምትሰማኘ የልቤ አምላክ፡፡
ከብዙ ዘመን በፊት ዛሬን አይተህ ሁሉን ያሰናዳህልኘ መድሃኒዓለም ሆይ አከብርሃለሁ፡፡ አለሙን አንድ ጊዜ አዳንከው እኔን ግን ስንት ጊዜ አዳንከኘ በእውነት አከብርሃለሁ፡፡

ስለወዳጆቼ ስለሰጠኸኘ በጎ በረከት ከልቤ አመሰግንሃለሁ፡፡ ሰማይና ምድርን ለምስጋና ደቦ ብንጠራ ለአንድ ቀን ውለታህን እንኳን ምላሽ አይሆንም፡፡ ሥራህን ሥራህ ያመስግነው፡፡

አንተ አንተ ነህ፡፡ አንተ አንተ ስለሆንክ እኛ እኛ ሆነናል ፈጥረህ እንዳልፈጠረ ማድረግ ስትችል ይኸው ቆመናል፡፡ ያንተ ከሆነው ምን ጎደለብን?? ሁሉን በቸርነትህ ሰፈርህልን፡፡ መስፈሪያህ ምህረት የሆነ ማንነቱን ላጣ ማንነት የሰጠህ አንተ ነህ፡፡

ትላንት ላይ ለዛሬ ቀጠሮ የያዝንብህ አድራሽ ጌታ አንተ ቸር ስለሆንክልን ነው፡፡ ዕለት ለማይገባን ይኸው ሳምንት ጨመርክልን ያንተ ስጦታ ምኑ ይነገራል፡፡

ተ
መ
ስ
ገ
ን

ሥሩ የበሰበሰ ዛፍ ከመውደቅ የሚያድነው የለም፡፡ አስተሳሰቡ የተበከለም መጨረሻው አሳዛኘ ነው፡፡ መለወጥ የሌለበት ጸጸት ጭቃ ላይ ተቀምጦ መታጠብ ነው፡፡ ደስታን ስትከተለው ይርቅኃል እግዚአብሔርን ስትከተል ግን ደስታ አንተን ይከተልሃል፡፡

ሰዎች ችግራቸውን የሚነግሩህ እንድትፈፅምላቸው ሳይሆን በአብዛኛው እንድናዳምጣቸው ነው፡፡ በሕይወትህ ትልቁ ባለውለታዎችህ የገፉህ ሰዎች ናቸው ባትገፋ ኖሮ ይህ እውቀትና ኑሮ አይኖርህም ነበር፡፡

መውደድህንና ምስጋናህን ቀጠሮ አትስጠው የምትወደውና የምታመሰግነው ሰው ያለው ቀን ዛሬ ብቻ ሊሆን ይችላልና፡፡

እሺ ካሉህ ይልቅ በጊዜው እምቢ ያሉህ ትልቅ ሰዎች ናቸው፡፡ አንድ ካላልክ ሁለት አትልም፡፡
ምቹ ጊዜን የምትጠብቅ ከሆነ ምንም አትሰራም ምቹ ጊዜ የመስራት ውጤት ነውና፡፡

ከወደዳችሁት ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጓቸው፡፡

አብይ የማርያም ልጅ ነኘ፡፡
@jahABP😊😊🙏🙏😍😍

ሳነብ ካገኘኀቸው መፅሀፍቶች ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንዲህ አቀረብኩት፡፡
07-01-2014

መልካም ምሽት ይሁንላቹ በሁሉ አመስግኑ፡፡
#ተመስገን

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →