TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #1904 828
AB PHOTOGRAPHY

#ንዒ_ኀቤየ( #ወደ_እኔ_ነይ )

በቀን ውስጥ ደጋግሜ የምጠራው ቃል ቢኖር ድንግል ሆይ ያንቺን አለም ላይ ካሉነገሮች ሁሉ ጣፋጭ የሆነውን ስምሽን ነው፡፡

ስላንቺ ምን ብለን እንደምንናገር ትልቁ ጭንቀታችን ነው፡፡

እናቴ ለዛሬ እኔነቴ ለዚህ ለመድረሴ ያንቺ ምልጃፀሎት አማላጅነት ነው፡፡ ትላንት እዛ ሆኜ ከኔ ጋር ነበርሽ ዛሬም አብረሽኘ አለሽ ሁሌም ታበረቺኛለሽ ሁሌም ጥንካሬን ጥሰጪኛለሽ ቀን ቀናት ወራት ወራትን አመት አመታትን ሲቆጥር የሔደው ሲሔድ አንቺ ሁሌም ከኔ ጋር ነሽ አይዞህ ትይኛለሽ፡፡


ትህትናሽ ትምህርት ቤቴ ነው እንደቃልህ ይደረግልኘ ብለሽ ለዓለሙ መድሃንን ሰተሻል እሳት የሆነውን በማህፀን ተሸክመሽ ለአለሙ ድህነትን ሰጥተሻል አግኘቼ እግሯን ባጠብኳት ብለሽ ትህትናን አስተምረሽናል በግብፅ በረሃ ረሀብን ጥምን ችለሽ ጥንካሬን አሳይተሽናል ከመስቀሉ ስር ተገኘተሽ በእናትነት ተሰጥተሽናል፡፡

ድንግል ሆይ አንቺ ትምህርት ቤታችን ነሽ ወዮዮዮ አንቺን ያላወቁ ፍቅርሽ እናትነትሽን አማላጅነትሽን ኧረ ስንቱን አጡ፡፡

አንቺ ለኛ የሰጠን የተመሰገነ ይሁን፡፡ለምሰራቸው ሀጢያቶች ይቅርታን ታሰጪኛለሽ ድጋሚ ከመሰናከል ትጠብቂኛለሽ የልቤን የማስበውን አንቺ ታውቂያለሽና መልካሙን እየሰጠሽ አሳድገሽ ይኸው ለዚ አብቅተሽኛል ይሔን ለአፍታም የማልረሳው ውለታሽ ነው፡፡

ዛሬ ላይ ቆሜ ትላንትን ሳስብ መኖሬ ይገርመኛል ያንቺ የልጅሽ ቸርነት ግን ይኸው አቁሞኛል እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ እባክሽ ዘመኔ በቤቱ ይፈፀም ዘንድ ለልጅሽ አሳስቢልኘ፡፡

ሞትሽ ሞታችን ትንሳኤሽ ትንሳኤአችን ነው፡፡

ጠላት ጠልፎ እንዳይጥለኘ
እባክሽን ድንግል ሆይ ከኔ አትለይ

@jahABP 16/12/13

#ንዒ_ኀቤየ( #ወደ_እኔ_ነይ)
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →