AB PHOTOGRAPHY
ቤተክርስቲያን ሔድኩ፡፡ እንደ እብድ ብቻዬን ማውራት ጀምሬ ነበር፡፡ ቀጥ ብዬ ዋናውን በር አልፌ ገባሁ፡፡ ትዝ ሲለኘ ለካ አልተሳለምኩም ተመልሼ ግራ ቀኘ በሩን ተሳለምኩ፡፡
ዘው አይባልም ዘሎ ፈጣሪ የተጎዳ ልቤን ቢመለከትም ቅሉ እዚህ ድረስ ልብ ውልቅ መሆኔ ለኔም ደግ አይደል፡፡
ወደ ውስጥ ስገባ የቤተክርስቲያኑ ድባብ የቤተመቅደሱ ወፋፍራም የጣውላ ከፈፎች ላይ የሰፈሩት ዋነሶች እድሜ ጠገቦቹ ዛፎች ከምንም በላይ ደግሞ ዝምታው ከውስጥ ብሶቴ ጋር ተዳምሮ እንባዬን አመጣው፡፡
ከምር የሰው ልጅ ምናምኒት አቅም እንደሌለው የሚያውቅበት የሆነ ጭብጦ ነገር መሆኑን የሚረዳበት ቦታ ቢኖር ቤተክርስቲያን ይመስለኛል፡፡
አሌክስ አብርሃም #ዙቤይዳ
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል
\\\ #ቦሌ_ሚካኤል\\\
Post #1903
816
