AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DEAIGN
ስራህ ቀላል ነው
"ከትላንት እንማራለን ዛሬን እንኖራለን ስለ ነገም ተስፋ እንዳርጋለን" በማለት የተናገረው አልበርት አንስታይን ነው፡፡
#የሰው_ልጅ_ትልቁ_ችግር_ከትላንት_መማር_አለመቻል_ነው፡፡
#ትላንት_የሚጠቅመን_ስንማርበት_ብቻ_ነው፡፡
ከትላንት መማር ከማልማት በላይ ነው፡፡
ሌላው የሰው ልጅ ችግር ዛሬን መኖር አለመቻል ነው፡፡ ስለ ትላንት በመቆጨት ስለነገ በመፍራት ዛሬን ያበላሻል፡፡
ስለትላንት መቆጨት የለብንም አናገኘውም ስለነገም አትጨነቅ ገና አልደረስክበትምና ዛሬን ግን ልንሰራበት ይገባል፡፡
#ሰለነገም_ተስፋ_ለማድረግ_የእምነት_ሀይል_ያስልጋል፡፡
አልበር አንስታይን ታላቅ የሒሳብና የፊዚክስ ሊቅ ነው፡፡ እርሱ ባገኘው የሒሳብ ቀመር ታላላቅ አገሮች በኒውክለር ኃይል ግዙፍ የኤሌትሪክ ጉልበቶችን ያንቀሳቅሳሉ፡፡ ታዲያ አንስታይን ኸአንድ ቀልደኛ ጋር ሲጓዝ ሰው ሁሉ ያን ቀልደኛ ፈርምልን ይለዋል፡፡ ያም ቀልደኛ አልበርት አንስታይንን፡- "እኔን ሰው ሁሉ ያውቀኛል" አለው
አንስታይንም "ስራህ ቀላል ስለሆነ ሁሉም ያውቅሃል አለው ይባላል፡፡"
ለዓለም የእውቀት ብርሃን ያመጡ ለአሰቃቂ በሽታዎችና ወረርሽኞች መድሐኒት ክትባት የፈለሰፉ ያለስቃይ ቀዶ ጥገናን ለማድረግ ማደንዘዣ የፈጠሩ ብዙም አይታወቁም፡፡ ለአገር ክብር ለወገን ነፃነት ለንጉስ ፍቅር በዳር ድንበር የሞቱ የሚስባቸው ጥቂት ነው፡፡ የሚታወቁት ቀለል ያለ ተግባር ያላቸው ወገኖች ናቸው፡፡ የአዋቂዎች ቀብራቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ በሕይወት ሳሉም የሚሸሻቸው እንጂ የሚቀርባቸው የለም፡፡
የብልግና መፅሐፍት ፍሬየሌላቸው ማዘናጊያ ጣቢያዎች የሐሜት ድህረ ገፆች ሁሉ ያውቃቸዋል፡፡ እውነትን የሚያስተላልፉ ጣቢያዎች ግን በፍፁም አይታወቁም፡፡
#ሰበር_ዜና_ተብሎ_መዓት_እንጂ_ምህረት_አይወራም፡፡
ሁሉም የመጣውን መዓት ለመስማት ይቸኩላል፡፡ ቀላል የሆኑ ነገሮች ሁሉ ያውቃቸዋል፡፡ የመረጃ እውቀት መደበኛ በእውቀት እየመሰላቸው ብዙዎች ተታለዋል፡፡
መረጃ አፈኛ ያደርጋል እውቀት ግን ጽሞናን ይሰጣል፡፡
አንደ ሰው "ቀልድ ማለት A እና Z ቦታ ሲለዋወጡ ማለት ነው፡፡ ፈረሱ ሰውዬውን ቢሸከመው አያስቅም ሰውየው ፈረሱ ቢሸከመው ግን ያስቃል፡፡ ቀልድ ማለት እንደዚህ ነው" ብሏል:: ፌዝና ቀልድ ከእውነት የሚያርቁ አደንዛዥ ሱሶች ናቸው፡፡ ሰው ከራሱ ጋር እንዳይገናኘ ለእውነት ዋጋ እንዳይከፍል የሚያዘናጉ ቀላል ነገሮች ናቸው፡፡
ብዙ ባለጠጎች ሊቅ ይዘው አይዞሩም አጫዋች ቀጥረው ግን ይዞራሉ፡፡ ብዙዎች እውቀት ለማግኘት ሳይሆን ታዋቂነትን ለማግኘት የማይሰራ ሥራ ይሠራሉ፡፡
#አዋቂና_ታዋቂ_መሆን_ልዩነት_አለው፡፡
አዋቂ መሆን በራስ ፊት ወጋ ማግኘት ነው፡፡ ታዋቂ መሆን በሌሎች ፊት ሙገሳ ማግኘት ነው፡፡ አዋቂ መሆን ጥረት ይጠይቃል ታዋቂ መሆን ማስታወቂያ መስራት በቂ ነው፡፡ አዋቂ ለመሆን አእምሮ ታዋቂ ለመሆን ገንዘብ ይጠይቃል፡፡ አዋቂ መሆን ብቸኛ ሊያደርግ ይችላል ታዋቂ መሆን ግን ጊዜያዊ አወዳሽ ያስገኛል፡፡
ሥራችን ፅኑ ከሆነ የሚያውቀን አይኖርም፡፡ ዓለሙ የሚያከብረው የራሱ የሆነውን ነውና መደሰት ይገባናል፡፡
#ሰው_ሁሉ_ይወደኛል_ማለት_ጅልነት_ነው፡፡
ግን ሁሉም ስለማይጠላን እግዚአብሔር ይመስገን፡፡
ሳነብ ካገኘሁት እንዲህ ለንባብ እንዲመች አድርጌ አቀረብኩላችሁ፡፡
@jahABP ነኘ መልካም ጊዜን እመኛለሁ ታዋቂ ለመሆን ሳይሆን አዋቂ ለመሆን እንጣር እላለሁ፡፡
አስተያየታችሁን አድርሱኘ😊🙏😍
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #1831
798