TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #1828 728
AB POHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ድርጅታዊ ወይስ አካላዊ???

ጋብቻ የእግዚአብሔር ስርዓት ነው፡፡ እግዚአብሔር ጋብቻን ሲመሰርት ድርጅታዊ አድርጎ ሳይሆን አካላዊ አድርጎ ነው፡፡

ጋብቻ ድርጅታዊ ሲሆንና አካላዊ ሲሆን ልዩነት አለው፡፡

ድርጅታዊ ግንኙነት መዋቅር እንጂ ህይወት የለውም፡፡ አካል ግን የተዋቀረ ህይወት ነው፡፡ ድርጅታዊ ግንኙነት ጥቅም እስከሰጠ ድረስ የሚቀጥል ነው፡፡ አካላዊ ግንኙነት ግን ደካማውን የሚሸከም ነው፡፡ ድርጅታዊ ግንኙነት ሁሉም የራስን ድርሻ ብቻ የሚፈፅምበት ነው፡፡ አካላዊ ግንኙነት ግን የራስን ድርሻ ፈፅሞ ፈፅሞ የሌላውን ማከናወን ነው፡፡ ድርጅታዊ ግንኙነት በጀት እስካለ የሚኖር ነው አካላዊ ግንኙነት በችግር ዘመንም አብሮ የሚካፈል ነው፡፡

ድርጅታዊ ግንኙነት መገማገገም ያለበት ነው አካላዊ ግንኙነት ግን መመካከር ያለበት ነው፡፡ ድርጅታዊ ግንኙነት አንዱ ያንዱ ቁስል የማይሰማው ነው አካላዊ ግንኙነት ግን ሕመም የጋራ ነው፡፡ ድርጅታዊ ግንኙነት ሙያን መስጠት የሚጠይቅ ነው፡፡ አካሌዊ ግንኙነት ግን ራስን መስጠት የሚጠይቅ ነው፡፡ ድርጅታዊ ግንኙነት ትክክለኛ የሀብት ክፍፍል ነው አካላዊ ግንኙነት ግን ሀብትን የናቀ ነው፡፡

ድርጅታዊ ግንኙነት ምን አለው? ይላል አካላዊ ግንኙነት ፍቅር አለ ይላል፡፡ ድርጅታዊ ግንኙነት በጉዳት በጡረታ የሚያበቃ ነው አካላዊ ግንኙነት ግን እስከ ሞት የሚዘልቅ ነው፡፡ ድርጅታዊ ግንኙነት ተጠያቂ ላለመሆን መጠንቀቅ ነው አካላዊ ግንኙነት ግን በጋራ ማስተካከል ነው፡፡

ጋብቻ ድርጅታዊ ሲሆን ጥቅምን ያሰላል የፉክክር ኑሮ ይሆናል በገንዘብ ላይ ይመሰረታል መካሰስ ይበዛበታል ጽንፍ ይይዛል ስለ ሀብት ብቻ ያስባል ምክንያት ፈላጊ ይሆናል፡፡


አካላዊ ሲሆን ደግሞ ምን አገኛለሁ? ሳይሆን ምን እሰጣለሁ? ይላል፡፡ የራሱ ድርሻ ፈፅሞ የሌላ ጉድለት ይሞላል ይሸፍናል ምስጢር ይጠብቃል ይታዘዛል አሳልፎም አይሰጥም ስለመብቱ አይሟገትም ሀብቴ ፍቅር ነው ይላል ከምክንያት በላይ በሆነ ፍቅር ይዋደዳል

#ጉድለትን_አሟልቶ_ያያል_የተሰበረውን_ቃል_ጠግኖ_ይሰማል፡፡


እግዚአብሔር የመሰረተው ወዳጅነት ቤተክርስቲያናዊ ትዳር አካላዊ ነው፡፡
ሕይወትና ደስታ ያለው በአካል ውስጥ ነው


እርሱ አካላዊ ግነኙነት ይጨምርልን፡፡😊🙏😍

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁነ አድርሱኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →