እነዛ እቅፋችን ውስጥ ሆነው እነቅልፍ የሚወስዳቸው ህፃናት😘 እነዛ ከትንሽነታቸው አንፃር ከፊት የሚሰለፉት ህፃናት እነዛ ከበሮ ለመምታት ጉልበትና አቅም የሌላቸው ህፃናት እነዛ ስንመጣ እግራችን ስር የሚጠመጠሙት ህፃናት እነዛ ቤተክርስቲያን ውሰዱን ብለው ሳንነሳ ለሊት በተኛንበት የሚከቡን ህፃናት እነዛ አቡነዘበሰማያትን በተኮላተፈ አንደበታቸው ይሉ የነበሩ ህዓናት እነዛ ድራማ ስንሰራ ቀድመው የሚስቁ ህፃና እነዛ መዝሙር ሳያልቅ እንቅልፋቸው የሚመጣ ህፃናት እነዛ ሲያጨበጭቡ እንኳ ድምፅ የሌላቸው ህፃናት እነዛ የትም ቦታ ሲያዩን እንደወንድማቸው የሚጠመጠሙብን ህፃናት እነዛ ስማችንን በጨለማ ይዘናቸው ስንሔድ ጅብ አይመጣብንም አይደል የሚሉት ህፃናት እነዛ በኮልታፋ አንደበታቸው ዝማሬን የጀመሩ ህፃናት እነዛ ፍቅር ብቻ ቀለባቸው የሆነ ህፃናት....😢😢😢😢😢😢😢😢😍😍😍😍😍
አሁን አድገውልን ጎርምሰውልን ያኔ ከነሱ በላይ የነበረውን ከበሮውን ተሸክመው እንደቅዱስ ዳዊት ሲመቱ ዝማሬውን በግሩም ሁኔታ ሲዘምሩት ጭብጨባቸው አገር ምድሩን ሲደበላልቀው ድራማውን የሚያስገርም አድርገው ሲያቀርቡት የኛ ያልነውን ስራ ቀጥ ለጥ አድርገው የኛን ፈለግ ተከትለው ማህበሩን በሀላፊነት ተረክበው ሲመሩት ካሳየናቸው ካስለመድናቸው መስመር እልፍ ሳይሉ አድገውልን ስማችንን ሳያስጠፉ ትልልቅ ልጆች ሆነውልን አምላከ ቅዱስ ዕራኤል የተባረከ ይሁንና እኛን እናመሰግናችኀለን ብለው ይኸው ድንቅ ፕሮግራም አዘጋጅተው የምስክር ወረቀት በሁሉም ሰው ፊት ሰጡን ምን እላለሁ በእንባ ከመሞላት ውጪ ከማልቀስ ውጪ ቃላት ይሔን ስሜቴን ይገልፁት ይሆን አይመስለኘም፡፡😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢
የድንግል ልጅ ክብር ይስጥልኘ ቅዱስ ዑራኤል ይጠብቃችሁ
አብይ የማርያም ልጅ የስነፅሁፍ ክፍል ሀላፊ🙏🙏🙏
Post #1825
716
